Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የዓመት በዓል ጓደኞች

ትኩስ ፅሁፎች

ጓደኛሞች አለን፡-

ዱሮ ለቅርጫና ለበግ ግዥ

እንቃጠር ነበር – እየጠጣን፡፡

ቀጥሎ ቅርጫው ቀረና፣

ለበግ ግዥ ብቻ እንገናኝ ጀመር፤

            እየጠጣን፡፡

ቀጥሎ ቀጥሎ፣ በግ ግዥው ቀረና፤

            ዶሮ ግዥ ገባን

            መጠጣትን እያሰብን፡፡

በሦስተኛው ቀጠሮ . . . ስለኑሮ ውድነት ልናወራ

                  በባዶ ሆድ ተገናኘን፡፡

‹‹ያገር ኢኮኖሚ አሪፍ ሆነልን!››

ብለን በምጸት ደመደምን፡፡

ከዚያ ወዲያ፣ ጓደኛ መሆን  አቆምን፡፡

  • ነቢይ መኮንን ‹‹ስውር ስፌት›› (2003)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች