Saturday, July 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

በጥል ከተሸነፍክ ሽንፈትህን መደበቅ አለብህ

ትኩስ ፅሁፎች

በአንድ ወቅት በኢታንግ መንደር ውስጥ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፡፡ ኦቢል ወደሚባለውም ጫካ በመሄድ እንስሳትን ማጥመድ ፈለጉ፡፡ ወጥመዱንም ካዘጋጁ በኋላ በእንስሳቱ መንገድ ላይ አኑረውት በማግስቱ ጠዋት የሆነውን ሊያዩ ሲመለሱ ወጥመዱ አንድ አንበሳ ቢይዝም አንበሳው ወጥመዱን ሰብሮ ማምለጡን አዩ፡፡

በዚህን ጊዜ አንበሳው በጣም ተናዶ ስለነበር በአቅራቢያው ሆኖ ይመለከታቸው ነበር፡፡ ቀስ ብሎ አድፍጦ ከጠበቃቸው በኋላ አጥማጆቹን ያሳድዳቸው ጀመር፡፡ እነሱም ሮጠው ሲያመልጡት አንበሳው ተመልሶ ወደ ጫካው ገባ፡፡

እነርሱም ወደ መንደራቸው በመመለስ ላይ ሳሉ “ይህንን ለማንም አንነግርም፡፡ አንበሳው ስላሸነፈን ሁሉም ይስቁብናል፤” ተባባሉ፡፡

የያዙትንም ዕቃ ሁሉ ቢላዎቻቸውን፣ ጦራቸውንና የውኃ ቅላቸውን ጭምር ጥለው ተመለሱ፡፡

“ፈሪዎች ናቸው ብለው ይሳለቁብናል፤” ተባባሉ፡፡

ነገር ግን ከቤታቸው ሲደርሱ በመንደራቸው ካለና መጠጥ ከሚሰጥበት አንድ ዛፍ ስር ሄዱ፡፡ የሚችሉትንም ያህል ከጠጡ በኋላ አንደኛቸው ብድግ ብሎ “ዛሬ ጠዋት አንበሳ አባሮን ንብረታችን ሁሉ ጠፋብን፤” ብሎ ተናገረ፡፡

ሁለተኛውም የጓደኛውን ትከሻ ነካ አድርጎ “አቁም! እባክህ ይህንን ለማንም አትንገር፤” አለው፡፡ ኦቢልም “መሽቷል፤” አለው፡፡

ይህንንም ያለው ኦቢል ጥቅጥቅ ያለ ጫካና ብዙ ምስጢሮችን የሚይዝ ነው ለማለት ፈልጎ ነው፡፡ ይህም ማለት በጥል ከተሸነፍክ ሽንፈትህን መደበቅ አለብህ ለማለት ነው፡፡

  • ኦፒው አምዎንግ ‹‹የጋምቤላ ተረት››
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች