Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና በታጣቂዎች ከታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 138ቱ ያህል መለቀቃቸው ተሰማ

 በታጣቂዎች ከታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 138ቱ ያህል መለቀቃቸው ተሰማ

ቀን:

ከአማራ ክልል ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም. የትምህርት ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ እያሉ፣ ከአዲስ አበባ በ155 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ገብረ ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል ከተባሉት ተማሪዎች መካከል 138ቱ መለቀቃቸው ተሰማ፡፡

ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርተር ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፣ 138 ተማሪዎች ከአጋቾች የተለቀቁት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ዘመቻ ሲሆን፣ 18 ተማሪዎች አሁንም በታጣቂዎች ታግተው እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ኢሰመኮ ስለታገቱት ተማሪዎች መረጃና አኃዝ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ማግኘቱንና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በሦስት አገር አቋራጭ አውቶቡሶች ውስጥ ተማሪዎችና ሌሎች መንገደኞች እንደነበሩ፣ ታጣቂዎቹ ተማሪዎቹን ከሌሎች መንገደኞች በመለየት እንዳገቷቸው የኢሰመኮ መረጃ ይጠቁማል፡፡

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በሰላም መሸኘቱን በመግለጽ መንገድ ላይ ተፈጠረ ስለሚባለው ጉዳይ መረጃው እንደሌለው ለሪፖርተር ገልጾ፣ ዕገታውን በተመለከተ ከማኅበራዊ የትስስር ገጾች መስማቱንና ለበላይ አካላት ሪፖርት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የተማሪዎችን ዕገታ አስመልክቶ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በኤምባሲው የትዊተር ገጽ ባሠፈሩት አጭር መግለጫ፣ ለገንዘብ ተብሎ ተማሪዎችንና ንፁኃንን ማገት ሊቆም ይገባል ብለዋል፡፡ ‹‹ባሳለፍነው ሳምንት ከ100 በላይ ተማሪዎችና መንገደኞች ለገንዘብ ሲባል ታግተዋል፤›› ያሉት አምባሳደሩ፣ ይህ ድርጊት ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አክለውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ ያሉ የዕገታ ወንጀሎች ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ግጭት፣ ምን ያህል ወንጀለኞችን እንደሚያበረታታና የሕግ የበላይነትን እንደሚያዳክም ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ሪፖርተር ለኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ በጉዳዩ ላይ ያለውን መረጃ ለማወቅ ላቀረበው ጥያቄ፣ ቢሮው ተፈጸመ ስለተባው የዕገታ ወንጀል የደረሰው ሪፖርትም ሆነ መረጃ አለመኖሩን በመግለጽ ድርጊቱ መፈጸሙን እንደማያውቅ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...