Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከአንድ ሚሊዮን በላይ ልጆችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማካካሻ ክትባት

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ልጆችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማካካሻ ክትባት

ቀን:

በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙና ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ አንድ ሚሊዮን ሕፃናትን ተጠቃሚ የሚያደርግና ለአሥር ቀናት የሚቆይ የማካካሻና የተደራሽነት የክትባት መርሐ ግብር በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ልጆችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማካካሻ ክትባት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

የጤና ሚኒስትር ደኤታ ደረጀ ድጉማ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ከሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳድሮች በመካሄድ ላይ ያለውን የክትባት መርሐ ግብር ተጠቃሚ የሚሆኑት ክትባት ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ ሕፃናት ናቸው፡፡

ከክትባቱም ቅድሚያ የሚሰጣቸው በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ ችግሮች ሳቢያ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች፣ እንዲሁም በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙና ወደ ቀድሞ ቀያቸው የተመለሱ ሕፃናት መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ከዚህም ሌላ ራቅ ባሉ ሥፍራዎች፣ ዝቅተኛ አፈጻጸም በታዩባቸውና በተለይም አርብቶ አደሩ አካባቢዎች፣ እንዲሁም ኩፍኝ፣ ኮሌራና ወባ የመሳሰሉ ወረርሽኞች በሚዘወተርባቸው ወረዳዎችና ከተሞች የሚገኙ ሕፃናት ቅድሚያ ከተሰጣቸው መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው በዚሁ መርሐ ግብር ላይ የሚሰጡት ወይም 14 ዓይነት ክትባቶች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም መካከል የፖሊዮ፣ ኩፍኝ፣ የሳንባና ከአንጀት ጋር የተያያዙ ክትባቶች ዋነኞቹ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ መርሐ ግብሩን ውጤታማ ለማድረግ የማካካሻ ፖሊሲና መመርያ መዘጋጀቱን፣ ክትባቱ ለሕፃናት ተደራሽ የሚሆነው በቋሚና በተንቀሳቃሽ ወይም በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎችና ክትባት በሚሰጡ ቡድኖች አማካይነት ነው፡፡ ለዚህም የሚያስፈልጉ የክትባት ግብዓቶች ከውጭ አገር ገብተው መሠራጨታቸውንና የጤና ባለሙያዎችም በመርሐ ግብሩ መሳተፋቸውን ሚኒስትር ደኤታው ገልጸዋል፡፡

ወላጆችና አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን ወደየጤና ተቋማቱ በማቅረብ የክትባቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ሚኒስትር ደኤታው አሳስበዋል፡፡

ከ40 ዓመት በፊት ከስድስት በማይበልጡ ክትባቶች የተጀመረው የክትባት መርሐ ግብር በአሁኑ ጊዜ ወደ 14 ዓይነት ክትባቶች ከፍ ብሏል፡፡ የተጠቀሰውም ቁጥር ለሴቶች፣ ለልጃገረዶችና ለአዋቂዎችም ጭምር የሚያገለግሉ እንደ ኮቪድ፣ የማሕፀን በር ካንሰር ወዘተ መከላከያ ክትባቶችንም ያካትታል፡፡

ሁሉም ክትባቶች ከውጭ አገር የመጡ ቢሆንም በአገር ውስጥ ክትባት የማምረት ጅማሮ መኖሩን ደረጀ (ዶ/ር) ጠቁመው፣ ይህንኑ ጅማሮ በማጠናከር ሕፃናቱ በአገር ውስጥ የተመረተ ደረጃውንና ጥራቱን የጠበቀ ክትባት ተጠቃሚ የሚሆኑበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...