Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅለካ ሞት ግጥም አይችልም

ለካ ሞት ግጥም አይችልም

ቀን:

እኔ እገጣሚው ለቅሶ ቤት

ልቤን ላነባ ስገባ

ሞትም ተከትሎኝ ገባ።

እኔ ወዲህ ማዶ ቆምኩኝ

እሱ ወዲያ ማዶ ቆመ

ከማህል ገጣሚው አለ።

ገጣሚው፣

የፊደል አርበኛ አይደለ? አስከሬኑ ጃኖ ለብሷል

ወንዝ አለት እንደሚንተራስ ብረት ሳጥን ተንተርሷል።

ሞትን ከገጣሚው ማዶ በስሱ በመገርመም ፎርም አሻግሬ እያየሁት

‹‹ለምን መጣህ?›› ብዬ ብለው

ሞት ፈጣጣው አፍ አውጥቶ፤

‹‹ግጥም ልማር›› አለኝ ኮርቶ፡

ይሄኔ…

አስከሬኑ ተግ አለና፣

ብድግ አለ ከተኛበት!

ሞትን በደም አይኑ አየና፡-

‹‹ሀጠራው!!›› አለ።

ቀጠለና… አምባረቀ!

‹‹ሞት ለዘለዓለም ይኑር!››

የሚል ሸቃባ መፈክር፣ እርኩስ ደረትህ ላይ ጽፈሕ

ግጥምን መማር ታስባለህ?

ግጥም የህያው ልሳን ነው፣ ለሞት አንደበት አይሆንም

የስንኝ ጠበል እሚፈልቅ በድን አለት ውስጥ አደለም

ግጥም ከነፍስ ቃል እንጂ፣ ከሥጋ ትንፋሽ አይነጥብም

አንዳች ሕይወትህ ውስጥ ሳይኖር፣ ፊደል በመቁጠር

አትገጥምም!

አንተ ግንዝ ነህ – ግዑዝ!

ባዶ ጥላ! ነብሰ – ከላ!

ሸቃባ! ልበ – ሽባ!

ዛሬ ደግሞ ብለህ ብለህ

ግጥም ልማር ብለህ መጣህ?!

ሀጠራው! ዓይን – አውጣ!

ውጣ!››

ይህን ሰምቶ መልስ ሲያጣ፤

ሞት የሚባለው ፈጣጣ

ጭራውን ሸጉቦ ወጣ!

ወይ ጉድ!

ስንቴ በኛ ቂም አርግዞ

ስንቱን ባለቅኔ ወስዶ፣ ስንቱን ቅኔ አጉዞ አጉዞ

‹‹ግጥም ልማር መጣሁ›› ይበል፣ ይሄ ሞት የሚባል ፉዞ!

ያውም ከማይጨበጠው፤

ከእሳት አበባው ወዳጄ

ከንጋት ግጥም አዋጄ

ከሞት ገዳዩ ቀኝ – እጄ?!

ግን ምን ደስ አለህ አትሉኝም?

ለካ ሞት ግጥም አይችልም!

ለካ ሞት ቅኔ አይገባውም!

– ነቢይ መኰንን የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅንን ዜና ዕረፍት ሲሰማ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...