Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ለስድስት ባለኮኮብ ሆቴሎች ዕውቅና ሰጠ

 የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ለስድስት ባለኮኮብ ሆቴሎች ዕውቅና ሰጠ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የአየር ብክለትን በመቀነስና በኃይል ቁጠባ አጠቃቀም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ስድስት ባለአራትና ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች የአረንጓዴ ካርድ ዕውቅና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

በመሀል ከተማ በሚገኙ አሥር ባለኮከብ ሆቴሎች የአካባቢ ብክለትን ከመቀነስ አኳያ እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦ መነሻ በማድረግ ዕውቅና መስጠቱን፣  የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለልኝ ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ ሆቴሎች ላይ በተደረገ ምዘና አብዛኛዎቹ የቱሪዝም ሚኒስቴር ያወጣውን አስገዳጅ ደረጃ ያላሟሉ መሆናቸውን አቶ ዋለልኝ ገልጸዋል፡፡

የውኃና የኤሌክትሪክ አጠቃቀም፣ የድምፅ ብክለት በመቀነስ፣ የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ በአግባቡ በማስወገድ፣ እንዲሁም የሚጠቀሙበትን ግብዓት መልሶ ጥቅም ላይ በማዋልና የሚጠቀሙት ግብዓት ብክለትን ከመቀነስ አኳያ ምን ይመስላል የሚሉትን መነሻ በማድረግ መሆኑን አቶ ዋለልኝ አስረድተዋል፡፡

ምልከታ ከተደረገባቸው አሥር ባለኮከብ ሆቴሎች የተሻለ አፈጻጸም አሳይተዋል የተባሉ ስድስት ሆቴሎች ዓርብ ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ከባለሥልጣኑ የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ሃያት ሬጀንሲ፣ ራዲሰን ብሉ፣ ጌትፋም ኢንተርናሽናል፣ ካፒታልና ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴሎች ባለአምስት ኮኮብ ሆቴሎች ሲሆኑ በአካባቢ ጥበቃና በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም የተሻለ አፈጻጸም አሳይተዋል ተብለው ዕውቅና የተሰጣቸው ናቸው፡፡

ግራንድ ኤሊያና ሆቴልና ማግሎኒያ ሆቴል ባለአራት ኮከብ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎች ሲሆኑ በተመሳሳይ ዕውቅና ከተሰጣቸው ሆቴሎች ውስጥ ተካተዋል፡፡

በሌላ በኩል አዚማን ሆቴል፣ ሳፋየር አዲስ ሆቴልና ደብረ ዳሞ ሆቴል በጥናቱ የተካተቱ ሲሆን መሥፈርቱን ባለማሟላታቸው ዕውቅና ሳይሰጣቸው የቀሩ ባለ አራት ኮከብ ሆቴሎች ናቸው፡፡

የቱሪዝም ሚኒስቴር የኮኮብ ደረጃዎችን ለመስጠት ሆቴሎችን የሚመዝንበትን ሒደት እንደተጠቀሙ የተናገሩት አቶ ዋለልኝ፣ ዕውቅና አሰጣጡ የመጀመሪያ ነው ብለዋል፡፡ 

ጥናት የተደረገባቸው ሆቴሎች የቱሪዝም ሚኒስቴር በዓለም ቱሪዝም ድርጅት ጥራት መመዘኛ መሥፈርት መሠረት አስገዳጂ መሥፈርቶችን አሟልተዋል ተብለው የኮከብነት ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆኑ፣ እንደ ስካይላይት ኢንተርናሽናል ሆቴልና እንደ ኃይሌ ግራንድ ያሉ ባለአምስት ኮኮብ ሆቴሎች በጥናቱ አልተካተቱም፡፡

በከተማዋ ያሉ ሁሉም ሆቴሎች የኃይል አጠቃቀም ቁጠባቸው በጣም ደካማ ነው ያሉት አቶ ደሳለኝ፣ ሆቴሎች በቀን ከፍተኛ የውኃ ፍጆታን ከመጠቀማቸው በላይ አማራጮችን ከመጠቀም ይልቅ ከኅብረተሰቡ ጋር እየተሻሙ ነው ብለዋል፡፡

ካፒታል ሆቴል የዝናብ ውኃን ለመጠቀም ሙከራ ያደረገ ብቸኛ ሆቴል እንደሆነ የተናገሩት ምክትል ሥራ አስኪያጁ፣ ተረፈ ምርታቸውን መልሰው ጥቅም ላይ የሚያውሉት ደግሞ  ምልከታ ከተደረገባቸው አሥር ሆቴሎች ሁለቱ ብቻ ናቸው፡፡

ለመታጠቢያና ለሌሎች አገልግሎት የተጠቀሙበትን ውኃ መልሶ ከመጠቀም አኳያ አንድ ሆቴል ብቻ መገኘቱን የጠቀሱት አቶ ደሳለኝ፣ ቀሪዎቹ ተጠቅመው እንደሚያስወግዱት ተናግረዋል፡፡

የተሰጣችው ዕውቅና ለአንድ ዓመት ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፣ በቀጣይ የአየር ብክለትን ከመቀነስና በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ የተሻለ አፈጻጸም ለሚያሳዩ ሆቴሎች፡ የጤና ተkማትና ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተkማት በየዓመቱ ዕውቀና እንደሚሰጣቸው ባለሥልጣኑ አስታውkል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...