Monday, July 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለ22 ዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የግብርና ናሙና ቆጠራ በመስከረም ወር እንደሚጀመር ተገለጸ

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • 62 ሺሕ ሠራተኞች በቆጠራው ይሳተፋሉ ተብሏል

የግብርናው ዘርፍ በአገር አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚው ላይ ያለውን አስተዋጽኦ በትክክል ለመለየት ያስችላል የተባለለት የግብርና ናሙና ቆጠራ፣ ከ22 ዓመታት በኋላ በ2017 በጀት ዓመት ከመስከረም ወር ጀምሮ ለአንድ ዓመት እንዲከናወን የጊዜ ሰሌዳ እንደተያዘለት ታወቀ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር በበላይነት የሚመሩት ከመንግሥት ተቋማት፣ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በተውጣጡ አባላት የተዋቀረው የግብርና ናሙና ቆጠራ ዓብይ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ካካሄደ በኋላ ነው ሚኒስቴሩ የቆጠራውን ጊዜ ይፋ ያደረገው።

እርሻና የእንስሳት ሀብትን ጨምሮ በግብርናው ዘርፍ ያሉ ሀብቶች በሙሉ የሚካተቱበት የናሙና ቆጠራው በሁሉም የአገሪቱ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚደረግ ሲሆን፣ ከመስከረም ወር ጀምሮ በሦስቱም የምርት ወቅቶች ማለትም በመኸር፣ በበጋ መስኖና በበልግ እንደሚካሄድም ታውቋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መረጃ ቆጠራው ከ22 ዓመታት በፊት ከሸፈነው ናሙና በተሻለ ሰፋ ተደርጎ እንደሚካሄድ የሚገልጽ ሲሆን፣ አነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶ አደሮች፣ በኢንቨስትመንት የሚለሙ ሰፋፊ እርሻዎችና በማኅበር የሚለሙ መሬቶች እንደሚካተቱ ተነግሯል።

ለቆጠራ ሥራው 62 ሺሕ ሠራተኞች እንደሚሰማሩ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በበኩሉ፣ የዝግጅት ሥራው መገባደዱን አስታውቋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች