Monday, July 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ቴሌ ቲቪ የተሰኘ የኦላይን ሲኒማ መተግበሪያ ይፋ ተደረገ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማበልፀግ የሚታወቀው ኤግላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ቴሌ ቲቪ የተሰኘ የኦላይን ሲኒማ መተግበሪያ ይፋ አደረገ፡፡

ኩባንያዎቹ በጋራ ያበለፀጉትን መተግበሪያ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረጉበት ወቅት፣ የተለያዩ ፊልሞችን ለተወሰኑ ቀናት በማከራየት ለአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንደሚያቀርቡና በፕሌይስቶር ወይም በአፕስቶር ማግኘት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ 

የኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በሱፈቃድ ጌታቸው መተግበሪያው ይፋ ሲደረግ እንደገለጹት፣ ፊልም የመከራየት ልምድን በቴክኖሎጂ በማዘመንና ፊልሞቹን በተገደቡ ቀናት በማከራየት ለተመልካቾች የሚያቀርብ አዲስ አሠራር ነው፡፡ አክለውም አሁን ያለውን የፊልም ኢንዱስትሪ የሚያነቃቃና ለተሻለ ተነሳሽነት የሚያነሳሳ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መተግበሪያው በማበልፀጉና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ በማድረጉ ሒደት አጋር የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ሰኢድ አራጋው በበኩላቸው፣ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በስልካቸው ኢንተርኔት ከመጠቀምና ከመደወል ባለፈ ሌሎች አገልግሎቶችን መጠቀም እንዲችሉ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ዓመታት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙን ያስታወሱት አቶ ሰኢድ፣ ከዚህ ቀደም ከነበሩት አገልግሎቶች በተጨማሪ በዲጂታል እየቀረቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከ78 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች፣ እንዲሁም ከ48 ሚሊዮን በላይ የቴሌብር ደንበኞች ያሉት ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኦላይን ሲኒማ መተግበሪያው ሲበለፅግ አጋር መሆኑ ደንበኞቹ ተጨማሪ አገልግሎቶችን እንዲያገኙና ፊልሞቹ ተደራሽ እንዲሆኑ ያግዛል ተብሏል፡፡

መተግበሪያውን በመጠቀም ፊልሞችን ለመከራየት የአገር ውስጥ ደንበኞች ቴሌብርን፣ ከአገር ውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ደግሞ በቪዛ፣ በማስተር ካርድና በአሜሪካ ኤክስፕረስ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች