Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበሒደት ላይ ያለው የአገር ውስጥ የጉበት ንቅለ ተከላ

በሒደት ላይ ያለው የአገር ውስጥ የጉበት ንቅለ ተከላ

ቀን:

ጉበት በሰው አካል ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነ አካል ነው፡፡ ለአጠቃላይ ጤና እና ደኅንነት አስፈላጊ የሆኑ ከምግብ የተገኙ ንጥረ ነገሮችን ማቀነባበር፣ ግሉኮስን እንደ ግላይኮጅንን ማከማቸትና የደም ስኳር መጠን መቆጣጠርን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ በውስጡ ባክቴሪያዎችንና ሌሎች የውጭ ብናኞችን ከደም ውስጥ ለማስወገድ የሚያግዙ ልዩ የመከላከያ ህዋሶችን መያዙ በሽታን ለመከላከል ይረዳል፡፡

ይሁን እንጂ በልዩ ልዩ በተፈጥሯዊም ሆነ በሰው ሠራሽ ምክንያቶች ጉበት ሊጠቃ፣ ሊጎዳ ይችላል፡፡ ከነዚህ አንዱ ‹‹ድምፅ አልባው ገዳይ በሽታ›› እየተባለ የሚጠራው ሄፕታይተስ  ቢ ነው፡፡ የጉበት ብግነት/መቆጣት የሚባለው ሄፕታይተስ የሰውን ጤንነት በእጅጉ ሊጎዳ የሚችለው አልኮል አብዝቶ በመጠጣት ወይም መርዛማ ለሆኑ ነገሮች በመጋለጥ ሳቢያ ሊመጣ ይችላል ይላሉ ባለሙያዎቹ።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የጉበት፣ ሀሞትና ቆሽት ቀዶ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት ውለታው ጫኔ (ዶ/ር) እንደሚያብራሩት፣  ጉበት በተለያዩ ምክንያቶች የሚጠቃ ሲሆን፣ አንደኛው ምክንያት ተፈጥሮአዊ ሌላው ምክንያት ደግሞ ተፈጥሮአዊ ያልሆነና በጊዜ ሒደት በተለያዩ የበሽታ ዓይነቶች የሚፈጠር ነው፡፡  

በርካታ ዓይነት ሄፐታይተሶች እንዳሉ ከእነዚህም ውስጥ ኬሚካልና ቫይራል ሄፐታይተሶች ተጠቃሽ እንደሆኑ ነው ያመለከቱት፡፡

‹ቫይራል ሄፐታይተስ› ማለት በቫይረስ ምክንያት የሚመጣና በጣሙኑም የሚታወቅ ነው፡፡ በአልኮል፣ በከፍተኛ የቅባት ወይም የስብ ክምችት፣ በአንዳንድ መድኃኒቶችና መርዛማ በሆኑ ኬሚካሎች አማካይነት ይከሰታል፡፡ በቫይረስ የሚመጣው በሽታ ብዙውን ቁጥር መያዙን ገልጸዋል፡፡

የጉበት፣ ሀሞትና ቆሽት ቀዶ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስቱ እንደሚያብራሩት፣ በተለያዩ በቫይረስ አማካይነት የሚመጡ የሄፐታይተስ ዓይነቶች ሲኖሩ እነዚህም ኤቢሲዲ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በብዛት በዓለም ላይ ተሠራጭተው በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱና ለጉበት ንቅለ ተከላ የሚዳርጉት ሄፐታይተስ ቢ ሲ በመባል የሚታወቁ ናቸው፡፡

በውለታው ጫኔ (ዶ/ር) አገላለጽ፣ ጉበቱ የተጠቃበት ሰው ጉበቱ ይወጣና የሌላ ሰው ጉበት ይተከልለታል፡፡ ይህም የሚሆነው በሁለት መንገድ ነው፡፡ አንደኛ ከቤተሰቡ ግማሽ ተወስዶ ለታካሚው ሊሰጥ ይችላል፡፡ ከዚህ አኳያ ሰጪውም ተቀባዩም የተቆረጠ ጉበት ነው የሚኖራቸው ከሦስት ወር በኋላ ግን የተቆረጡት አድገው ወደ መደበኛ ቅርፃቸው ይመለሳሉ፡፡ ንቅለ ተከላው ለብዙ ታካሚዎች ዕድሜ እንዲረዝም አድርጓል፡፡

የአውሮፓና የእስያ አገሮች የጉበት ንቅለ ተከላ ሥራ ላይ ከዋለ ስድሳ ዓመት እንደሆነው፣ በአፍሪካ ከሰሃራ በታች ካሉ አገሮች ከደቡብ አፍሪካ ውጪ የሚሰጥበት አገር እንደሌለ የተናገሩት ባለሙያው፣ በኢትዮጵያም የጉበት ንቅለ ተከላ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ ከሰሃራ በታች ባሉት አገሮች ውስጥ  በሄፒታይተስ የሚጠቁ ከፍተኛ ቁጥር ያለባት አገር እንደሆነች ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ብዙ ምክንያቶች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ መረጃው እንደሚጠቁመው ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ከአሥር ሰዎች አንዱ በተለይ በሄፐታይተስ ‹‹ቢ›› ከሦስት እስከ አራት ያሉ ደግሞ ሄፐታይተስ ‹‹ሲ›› አለባቸው፡፡

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ከሚመጡት ታካሚዎች መካከል በርካታዎች በሄፐታይተስ የተጠቁ መሆናቸውን፣ ይህም ሆኖ ግን የሄፐታይተስ ተጠቂዎች ሁሉ ንቅለ ተከላ ሕክምና ያስፈልጋቸዋል ማለት እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

በሆስፒታሉ እንደታየው ከሆነ ከአሥር ታካሚዎች ከአራት እስከ ስድስት የሚደርሱ ንቅለ ተከላ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡

የብዙ ታማሚዎችን ሕይወት ለመታደግ የሕክምና ኮሌጁ የጉበት ንቅለ ተከላ ሕክምናን ለማስጀመር የሚያስችሉ ሥራዎችን እያካሄደ መሆኑን፣ አንዱ ኮሌጁ ከሚያስገነባቸውና አፈጻጸማቸው 90 በመቶ ከደረሱት ሦስት ግዙፍ ሕንፃዎች መካከል አንዱን ሕንፃ ለንቅለ ተከላ ሕክምና አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል፡፡

ባለ ስምንት ፎቁ ሕንፃ አምስት የቀዶ ሕክምና ክፍሎች ያሉት ሲሆን  በአንድ ጊዜ አንድ መቶ ሰባ ታካሚዎችን ማስተናገድ እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡

የሠለጠነ የሰው ሀብት ልማት በማፍራት ረገድም ለንቅለ ተከላ ሕክምና ቅርብ የሆኑ ባለሙያዎችን ማዘጋጀት እንደተቻለና ለእነዚህም ባለሙያዎች ከዘጠኝ ወር እስከ አንድ ዓመት ተጨማሪ ሥልጠና ከተሰጣቸው ንቅለ ተከላ ማከናወን ይችላል ተብሎ እምነት እንዲታጣለባቸው ከሰብ ስፔሻሊስቱ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...