Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየክለቦች የፋይናንስ አስተዳደር መመርያ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እንዲወስኑበት ሊደረግ ነው

የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደር መመርያ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እንዲወስኑበት ሊደረግ ነው

ቀን:

  • ፕሪሚየር ሊጉ ቅዳሜ ፍፃሜውን ያገኛል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ከተቋቋመባቸው መሠረታዊ መርሆዎች አንዱ፣ ክለቦቹ አሁን ከሚገኙበት የፋይናንስ (ገንዘብ) ጥገኝነት ተላቀው ራሳቸውን እንዲችሉ ማስቻል ነው፡፡ በዚህ ሳይወሰንም ያላቸውን ፋይናንስ በሕጋዊ አግባብ እንዲጠቀሙ ማድረግ አንዱ ግቡ ቢሆንም፣ ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀው የፋይናንስ አስተዳደር መመርያ ግን እስካሁን ሳይተገበር ቆይቷል፡፡

የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደር መመርያ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እንዲወስኑበት ሊደረግ ነው | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ችግሩን መፍታት ይቻል ዘንድ በቅርቡ በአክሲዮን ማኅበሩ የተዘጋጀው ረቂቅ የፋይናንስ አስተዳደር መመርያ፣ ማኅበሩን ጨምሮ በክለቦችና ሌሎችም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት መክረውበት እንዲፀድቅ ከተደረገ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጡበት ይደረጋል ተብሏል፡፡

ከአራት ዓመታት በፊት በውዝግብና ክርክር ውስጥ አልፎ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር፣ ክለቦች ዘላቂ የሀብት ምንጭ እንዲኖራቸው ከሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን ሊጉ ቀጥታ ሥርጭት እንዲኖረው ከደቡብ አፍሪካው የዲኤስ ቲቪ ካምፓኒ ጋር የአራት ዓመታት ኮንትራት መፈራረሙ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ይህ ኮንትራት ሊጠናቀቅ የቀረው የአንድ ዓመት ጊዜ ብቻ ሲሆን፣ ዲኤስ ቲቪ ኮንትራቱን ያድሳል? ወይስ ያቋርጣል? የሚለው እስካሁን አልታወቀም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አክሲዮን ማኅበሩ ስለጉዳዩ ካምፓኒው ኮንትራቱን በተመለከተ ምንም ያለው ነገር ባለመኖሩ እየጠበቀ መሆኑ መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በአክሲዮን ከመደራጀታቸው በፊት ተጠያቂነትና ግልጽነት በሌለው የፋይናንስ ሥርዓት መቆየታቸው፣ በተለይ የከተማ ከንቲባ የሚያስተዳድራቸው ክለቦች በነበረው የአሠራር ሥርዓት በጀትን በሕጋዊ አግባብ ባለመጠቀም የመንግሥት ቋት ጠባቂ ሆነው እንዲቆዩ አድርጓቸው ቆይቷል፡፡

ይህም ሆኖ በአክሲዮን ማኅበሩ አማካይነት ተዘጋጅቶ ሕጋዊ ዕውቅና ኖሮት ሥራ ላይ እንዲውል ሲደከምበት የቆየው የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደር መመርያ ተግባራዊ እንዳይደረግ የክለቦች አስተዳደሮች በአንድም ሆነ በሌላ እንከን እየተፈለገ እንዲጓተት ምክንያት ሆኖ እንዲቆይ ማድረጉ እንዳልቀረ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደር መመርያ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እንዲወስኑበት ሊደረግ ነው | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ከከተማ ከንቲባዎች የገንዘብ ድጎማ የማይደረግላቸው ጥቂት ክለቦች ካልሆኑ፣ ብዙዎቹ ክለቦች በአክሲዮን ማኅበሩ ተዘጋጅቶ በብዙ መድረኮች ለውይይት ቀርቦ መፅደቁ የተረጋገጠው፣ የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደር መመርያ፣ እንደገና ከሁለት ሳምንታት በኋላ በአዲስ አበባ በሚደረግ ውይይት የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥበት ቀጠሮ ተይዟል፡፡ የክለቦቹን በጀት በተፈለገው ሁኔታ ለመጠቀም ፍላጎት ያላቸው በከተማ አስተዳደር ስም በሥራቸው ለሚቋቋሙ ክለቦች ከበጀት ጀምሮ ይሁንታ የመስጠትም ሆነ የመንሳት ልምድ የነበራቸው ስለመሆቸው ጭምር እየተነገረ ይገኛል፡፡

በጉዳዩ ቁርጠኛ አቋም ይዞ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር፣ የፋይናንስ አስተዳደር መመርያው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን የሚያስተዳድሩ የከተማ አስተዳደር በተለይም ከንቲባዎች፣ የክለብ ፕሬዚዳንቶችና አመራሮች፣ እንዲሁም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በሚገኙበት ጉዳዩ ለውይይት ቀርቦ መመርያው ከ2017 ዓ.ም. የውድድር ዘመን ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ፣ የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ በተለይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ፍፃሜውን ያገኛል፡፡ ሊጉን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ክለብ በ61 ነጥብና ከሰሞኑ 80ኛ የምሥረታ ክብረ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች ያከበረው የመቻል እግር ኳስ ክለብ፣ በ60 ነጥብ በአንድ የነጥብ ልዩነት ተቀዳድመው የመጨረሻውን ቀን እየጠበቁ ናቸው፡፡

በ30ኛው ሳምንት መቻል ከአዳማ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ ወደ ብሔራዊ ሊግ መውረዱን ካረጋገጠው ሻሸመኔ ከተማ ጋር በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የ2016 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሚለይ ይሆናል፡፡ አሸናፊው ክለብ በ2017 የውድድር ዘመን ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ይወክላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...