Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹መቻል ለኢትዮጵያ››

ትኩስ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ እግር ኳስም ሆነ በሌሎች ስፖርቶች ታሪክ ሁነኛ ስፍራ ያለው፣ የምሥረታውን 80ኛ ዓመት እያከበረ ያለው መቻል ስፖርት ክለብ ነው፡፡ በመከላከያ ሠራዊት ሥር ያለው መቻል፣ በ1936 ዓ.ም. ሲመሠረት የእግር ኳስ ክለቡ ‹የጦር ሠራዊት› በሚለው ስያሜ ለተወሰኑ ዓመታት ከቆየ በኋላ ‹መቻል› የሚለውን ስም መጠቀም ጀምሯል፡፡ ድኅረ አብዮት እስከ ዓምና ይታወቅበት የነበረው ስሙ ‹ምድር ጦር› ቢሆን፣ ዘንድሮ ግን የቀደመ ስሙን መቻልን አምጥቶታል፡፡ ክብረ በዓሉን ከሰኔ መባቻ ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ሲሆን፣ ባለፈው እሑድ (ሰኔ 23) መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የጎዳና ሩጫ ውድድር አከናውኗል፡፡ የተለያዩ ክለቦች በተወዳደሩበት፣ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በሴቶች መቅደስ ሽመልስ፣ በወንዶች ደግሞ በላይ ዝቁ አሸናፊዎች ሆነዋል። ፎቶዎቹ ሁነቱን ያሳያሉ፡፡

‹‹መቻል ለኢትዮጵያ›› | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር‹‹መቻል ለኢትዮጵያ›› | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

– ፎቶ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች