Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየግል ሚዲያዎች በፌዴሬሽን ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባዔና በፓርላማው የበጀት ውይይት ላይ እንዳይገቡ...

የግል ሚዲያዎች በፌዴሬሽን ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባዔና በፓርላማው የበጀት ውይይት ላይ እንዳይገቡ ተከለከሉ

ቀን:

የአገሪቱ ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሆኑት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት በየራሳቸው የስብሰባ አዳራሾች በሚያካሂዷቸው ስብሳባዎች፣ የግል መገናኛ ብዙኃን ገብተው እንዳይዘግቡ ተከለከሉ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ከሰኔ 24 ቀን ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በምክር ቤቱ ግቢ ዓመታዊ ጉባዔውን ያካሄደ ሲሆን፣ ምክር ቤቱ ጥሪውን ለተመረጡ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ብቻ በማስተላለፍ የግል መገናኛ ብዙኃን እንዲገቡ አልተፈቀደላቸውም፡፡

ምክር ቤቱ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርጋቸውን ስብሳበዎች የግል ሚዲያ ተቁማት አለመጠራታቸውን በማንሳት ቅሬታ ሲያቀርቡ መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡  በዚህ ስብሳባ ለመሳተፍ ወደ ምክር ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ገብቶ የነበረው የሪፖርተር ጋዜጣ ባልደራባ አዳራሽ ለቆ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

የፌደሬሽን ምክር ቤት ሰሞነኛ ጉባዔው የ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርትን ያደመጠ ሲሆን፣ በተለይም የመንግሥታት ግንኙነት፣ የዴሞክራሲ አንድነትና የሕገ መንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ፣ የማንነት የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ፣ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴና የሕገ መንግሥት ትርጉምና የውሳኔ አፈጻጸም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡

በዚህ ዓመታዊ ጉባዔ ከቀረቡት ሪፖቶች መካከልና ሪፖርተር ያገኘው ሰነድ እንደሚያሳው፣ የወልቃይት፣ የራያና ጠለምት ማኅበረሰቦች ያቀረቧቸውን የማንነት ይታወቅልኝ ጥያቄዎች በተመለከተ ለውሳኔ ሒደት የሚያስፈልጉ የቅደመ ሁኔታዎች ሥራዎች የተሠሩ ቢሆንም፣ በፀጥታ ችግር ምክንያት ቦበታው ተገኝቶ መረጃ ለማሰባሰብ አለመቻሉ ተገልጿል፡፡ በቀጣይ የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ሲሻሻል በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው መደበኛ ስብሳባ ለተመረጡ የመንግሥት ሚዲያዎች ብቻ ጥሪ ያስተላለፈ ሲሆን፣ ምክር ቤቱ ጥሪ ያላደረገላቸው የግል የሚዲያ ተቋማት ሁኔታውን ለመዘገብ በቦታው ቢገኙም እንዲገቡ አልተፈቀዳላቸውም፡፡  ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ማብራሪያ የጠየቃቸው የሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ምሥራቅ መኮንን፣ ‹‹እኛ አልከለከልንም፣ ስብሳባ በዝግ አላካሄድንም›› የሚል ምላሽ ከሰጡ በኋላ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ ቢሞከርም ስልካቸውን ዘግተዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባው ሁለት ኢሚግሬሽንን የሚመለከቱ ረቂቅ አዋጆችና በኢትዮጵያና በኩዌት መካከል በሥራ ሥምሪት ዘርፍ የተፈረመ የመግባቢያ ሰነድ ለማፅደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ማፅደቁን፣ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ በተጨማሪም በፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት አመዳደብና አስተዳደር ላይ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጋር በዝርዝር ስለመወያየቱ ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...