Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያና ሶማሊያ አለመግባባታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቀጠሮ መያዛቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ አለመግባባታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቀጠሮ መያዛቸው ተገለጸ

ቀን:

ኢትዮጵያና ሶማሊያ፣ ከሶማሌላንድ ጋር በተደረገ በወደብ ስምምነት ምክንያት በመሀላቸው የተፈጠረውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ ለነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ቀጠሮ መያዛቸው ተገለጸ፡፡

በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋባዥነት ወደ ዋና ከተማዋ አንካራ የተጓዙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀ ሥላሴ (አምባሳደር) እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም፣ ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ካደረጉት ወይይት በኋላ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በቱርክ የተካሄደው ውይይት፣ ለሁለቱ አገሮች አለመግባባት መፍትሔ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ግልጽና ወዳጅነት የተሞላበት የሐሳብ ልውውጥ መደረጉን አስታውቋል፡፡

ሁለቱ ሚኒስትሮች በአገሮቹ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ዕልባት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸውን የጠቀሰው መግለጫው፣ መልካም ጉርብትናና ቀጣናዊ መረጋጋትን ከግምት ውስጥ በማስገባት መፍትሔዎችን ለማመላከት ያለሙ ውይይት እንደተደረገ ገልጿል፡፡

በሁለቱ አገሮች መካከል ለተፈጠረው አለመግባባትና የዲፕሎማሲ አታካራ መነሻ ለኢትዮጵያ የባህር በር ያስገኛታል የተባለለት የመግባቢያ ስምምነት፣ የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት ከስድስት ወራት በፊት በማድረጋቸው ምክንያት መሆኑ ይታወሳል፡፡

ከሁለቱ አገሮች ንግግር በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን፣ አገራቸው ከሁለቱ አገሮች ጋር ባላት የቆየና ሰፊ ትብብር፣ ይህንን የአስማሚነት ሚና መጫወት እንዳለባት ታምናለች ብለዋል፡፡ ሁለቱ አገሮች ወደፊት በአንካራ ተገናኝተው እንደሚወያዩም አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...