Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየዳያስፖራውን እንግልትና ተግዳሮት ይቀርፋል የተባለ መመርያ መዘጋጀቱ ተገለጸ

የዳያስፖራውን እንግልትና ተግዳሮት ይቀርፋል የተባለ መመርያ መዘጋጀቱ ተገለጸ

ቀን:

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ሁሉም የመንግሥት ተቋማት የዳያስፖራውን ተሳትፎ እንዲያሳድጉና ቅንጅታዊ አሠራርን እንዲከተሉ የሚያስችል፣ የዳያስፖራውን እንግልትና ተግዳሮት ይቀርፋል የተባለ መመርያ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

ተቋሙ ይህንን የገለጸው በዘንድሮ በጀት ዓመት ከዳያስፖራ ማኅበረሰብ ልማትና ተሳትፎ ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ሥራዎችን ከሰኔ 22 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ሲያካሂድ ነው፡፡

በዳያስፖራ አገልግሎት የዳያስፖራ ተሳትፎና መብት ዳይሬክተር አቶ አውላቸው ማስሬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የመንግሥት ተቋማት የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሠራር መከተል ይኖርባቸዋል፡፡

በተለይ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ ባንክ፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ሌሎች የመንግሥት ተቋማት ምን መሥራት አለባቸው? ለሚለው በመመርያው ውስጥ መቀመጡን አክለው ገልጸዋል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት እንግልት እንደሚገጥማቸው ጠቅሰው፣ ተቋማቱ ተናበው እንዲሠሩና ያሉትን ችግሮች እንዲቀርፉ በመመርያው ውስጥ የተለያዩ ጉዳዮች መካተታቸውን ተናግረዋል፡፡

‹‹ቅንጅታዊ አሠራር›› የሚል ስያሜ የተሰጠው መመርያውም፣ እያንዳንዱ ተቋም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ተወጥቷል ወይ? ካልሠራስ ምን ይደረጋል? የሚለውን ለማወቅ በየወሩ ግምገማ የሚካሄድ መሆኑን የሚገልጽ ክፍል ማካተቱን አስረድተዋል፡፡

ሁሉም ጉዳዮች የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ በአንድ ተቋም ብቻ የማይቻል መሆኑን ታምኖበት ወደዚህ አሠራር መገባቱን ገልጸው፣ ይህ አሠራር ከዚህ በፊት ያልተለመደና የመጀመሪያ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የዳያስፖራው ተሳትፎ እንዲያድግ የተሠሩ ሥራዎች ምንድናቸው? ያጋጠሙ ችግሮችስ? የሚሉትን በውይይቱ ወቅት በዝርዝር መነሳቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በወቅቱም ዳያስፖራው ኢንቨስትመንት ተሳትፎ ሲያደርግ በወቅቱ ውሳኔ የማግኘት ችግር፣ የመሬትና የብድር አቅርቦት ውስንነትና ሌሎች ችግሮች ታይተዋል ብለዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታትና ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ምን መደረግ አለበት የሚለው ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ መግባባት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ በሁሉም ጉዳዮች ተሳትፎ አድርገው የራሳቸውን አሻራ እንዲጥሉ ለማስቻል ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው ያሉት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ጥናት የባለድርሻ አካላት አስተባባሪ አቶ ጥበቡ ታፈሰ ናቸው፡፡

በዘንድሮ በጀት ዓመት የተደረጉ ውይይቶችን እንደ መነሻነት በመጠቀም፣ ለመጪው ዓመት የተለያዩ ዕቅዶችን ለማዘጋጀት ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዳያስፖራ ፖሊሲ ጋር ተያይዞ ያሉ የሕግ ማዕቀፎች፣ የአገልግሎት አሰጣጦች፣ እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች መፍትሔ ለማበጀት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

ለውይይቱ በዘርፉ የተከሰቱ መልካምና መጥፎ ጎኖችን በመለየት፣ ለወደፊቱ የዳያስፖራው ማኅበረሰብን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንዴት ማስተናገድ አለብን የሚለው ጉዳይ መለየቱን አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...