Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዩኒቨርሲቲዎች የቀጣይ ዓመት የምግብ በጀት ካልተስተካከለላቸው ተማሪዎችን መቀበል እንደማይችሉ አስታወቁ

ዩኒቨርሲቲዎች የቀጣይ ዓመት የምግብ በጀት ካልተስተካከለላቸው ተማሪዎችን መቀበል እንደማይችሉ አስታወቁ

ቀን:

  • ማረሚያ ቤቶችም ታራሚዎችን መመገብ እንደከበዳቸው ተነግሯል

በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በመንግሥት ተገንብተው ተማሪዎችን በራሳቸው ወጪ እያስተናገዱ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች፣ እንዲሁም የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በቀጣይ ዓመት የሚመደበው የምግብ በጀት ካልተስተካከለ ምግብ ማቅረብ አዳጋች እንደሚሆንባቸው አስታወቁ፡፡ ዩኒቨርሰቲዎች ተማሪ ለመቀበል የማይችሉበት ደረጃ እንደሚደርሱ ተናግረዋል፡፡

መንግሥት በየዓመቱ መጨረሻ ለመጪው በጀት ዓመት ለተቋማት የሚደለድለውን ዓመታዊ በጀት ተከትሎ፣ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ጥያቄ ሲያቀርቡበት የኖረውና ለአንድ ተማሪ የሚመደብ የአንድ ቀን ወጪ 22 ብር እስካሁን መልስ ማግኘት አልቻለም፡፡ በተመሳሳይ በማረሚያ ቤቶች ለታራሚዎች የሚቀርበው ገንዘብ በቂና ጥራት ያለው ምግብ ለማቅረብ መቸገራቸውን ገልጸዋል፡፡

ከሰሞኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ለ2017 በጀት ዓመት በደለደለው የ971 ቢሊዮን ብር የበጀት ዕቅድ የተለያዩ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) ባነሱት ጥያቄ፣ ለ2017 በጀት ዓመት የቀረበው በጀት በድጋሚ ጥያቄ የማይቀርብበት መሆኑን ገንዘብ ሚኒስቴር የተናገረ ቢሆንም ቀድሞ በነበረው በጀትና በ22 ብር የአንድ ተማሪ ቁርስ ምሳና እራት መድቦ ማስተናገድ በከፍተኛ ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ በርካታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች በተገኙበትና ለመጠየቅ ዕድል ባላገኙበት መድረክ ዕድል አግኝተው የጠየቁት ለሚ (ዶ/ር)፣ የተማሪ ቀለብ በጀት መፍትሔ ካልተበጀለት በቀር በ2017 ዓ.ም. ተማሪን ተቀብሎ ለማስተማር በከፍተኛ ሁኔታ አስቸጋሪ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ በመሆኑም መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጥናት እያደረገ መሆኑን ስለመስማታቸው ጠቅሰው፣ የተጀመረው ጥናት ተጠናቆ አስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጠው የመማር ማስተማሩ ሒደት አዳጋች ይሆናል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ሁሴን ዑመር (ዶ/ር) በሰጡት አስተያየት፣ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ያለው ችግር የተመደበው 22 ብር አነስተኛ ከመሆኑ ባሻገር፣ አካባቢው በረሃ በመሆኑ መምህራንና ሌሎች አካላት የሚሰጣቸው የበረሃ አበል የሚታሰብ ቢሆንም፣ ለተማሪዎች ምግብ በጀት ላይ ግን የማይታሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ የበረሃ አበል አለመጨመር አነስተኛ የሆነውን 22 ብር በጀት ከሞቃታማው ተፈጥሮ ጋር እየተጋፉ የሚማሩ ተማሪዎች ኑሮዋቸውን አዳጋች አድርጎታል ይላሉ፡፡ የተማሪዎች 22 ብር የቀን አበል ላይ የበረሃ አበል ቢጨምርም ያን ያህል ለውጥ ያመጣል ተብሎ ባይጠበቅም በተወሰነ መልኩ ግን ችግሩን ሊያቀለው እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ተማሪዎች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መቋቋም እያቃታቸው ነው ያሉት ሁሴን (ዶ/ር)፣ በቀጣይ ይህን ችግር በመቋቋም መቀጠል የማይቻል በመሆኑና እየከበደ በመምጣቱ ምክር ቤቱ ትብብር አድርጎ መፍትሔ ይስጠን ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በፍትሕ ሚኒስቴር የሀብት አስተዳዳር ዋና ዳይሬክተር አቶ የኋላሸት አግዝ በሰጡት አስተያየት፣ የክልል ማረሚያ ቤቶች ላይ የምግብ ሁኔታው እየተስተካከለ ቢመጣም፣ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ችግሩ ባለበት ቀጥሏል ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት፣ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ እንዳለው ችግር ሁሉ ታይቶና ተጠንቶ መፍትሔ እንዲሰጥ ቋሚ ኮሚቴው ያግዘን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አክለውም ለታራሚዎች ምግብ ማቅረብ አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸው፣ ማሻሻያ የሚደረግ ከሆነ ጉዳዩ ሄዶ ሄዶ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊሆን ስለሚችል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ጉዳዮች አማካሪው አቶ ተፈራ ደመቀ በሰጡት መልስ፣ የአገሪቱ በጀት ውስን ስለመሆኑ ጠቅሰው ይህን ውስን ሀብት ከፍላጎት ጋር ማጣጣም ያስፈልጋል ብዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተማሪዎች ቀለብ አነስተኛ መሆኑ የሚታወቅ ጉዳይ እንደሆነና ይህን ለማሻሻል የትምህርት ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ስታስቲክስ አገልግሎት ጋር በመሆን ጥናት እየተካሄደበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በጥናቱ ውጤት መሠረት የመንግሥትን አቅምና አሁን ያለውን የዋጋ ግሽበት በማጣጣም የሚሠራ ይሆናል ብለዋል፡፡  በመጪው ዓመት የትምህርት ካላንደሩ ከመጀመሩ በፊት ጥናቱ ተጠናቆ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚቀርብና በምክር ቤቱ ውሳኔ ከተሰጠበት በኋላ በመጠባበቂያ በጀት ይሸፈናል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በማረሚያ ቤትና በሆስፒታሎች ተኝተው ለሚታከሙ ለአልጋ የሚሰጠው ተመን በጥናት ላይ ተመሥርቶ በሚደረግ ማሻሻያ፣ የተመን ለውጥ ለማከናወን ጥናቱ በመንግሥት ቀርቦ የሚሻሻል ይሆናል ብለዋል፡፡ ይህንንም የማሻሻል ሥራ ግድ የሚል በመሆኑ ከ2017 ጀምሮ የሚስተካከል ይሆናል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...