Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየቤት ሠራተኞች ሕጋዊ የሰነድ ውል እንዲኖራቸው የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሊዘጋጅ ነው

የቤት ሠራተኞች ሕጋዊ የሰነድ ውል እንዲኖራቸው የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሊዘጋጅ ነው

ቀን:

የአገር ውስጥ የቤት ሠራተኞች ከአሠሪዎቻቸው ጋር ሕጋዊ የሰነድ ውል እንዲኖራቸው ጥናት በማድረግ፣ የሕግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

 ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው ለዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመ ክርስቲያናዊ ድርጅት የቤት ሠራተኞች የሥራ ላይ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታን አስመልክቶ፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ የሥራ ሁኔታቸውን በሕግ የሚደነግግ ደንብ እስኪወጣ ድረስ፣ በመንግሥት ደረጃ ተቀባይነት ያለው የሥራ ቅጥር ውል ለመንደፍ የሚያስችል ውይይት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲያካሂድ ነው፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የሦስትዮሽ ግንኙነት ማስተግበሪያ ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳልክ ተክለ ሃዋሪያት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የቤት ሠራተኞች ከአሠሪዎቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ጤናማ እንዲሆንና መብቶቻቸው እንዲጠበቁ ለማድረግ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡

የቤት ሠራተኞች መብቶቻቸውንና ግዴታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲለዩ እንዲህ ዓይነት አሠራር መከተል አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት ገልጸው፣ ማናቸውም የቤት ሠራተኞች ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ አገር የሥራ ሥምሪት በበቂ ሁኔታ እንዲሠለጥኑ ሚኒስቴሩ የተሻለ አሠራርን ዘርግቶ ወደ ሥራ መግባቱን አክለዋል፡፡

በቅርቡም ጥናት ተደርጎበት ወደ ሥራ የሚገባበት ይህ አሠራር ለውጭ አገር የሥራ ሥምሪት መነሻነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የገለጹት ኃላፊው፣ ጥናቱንም ከዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመ ክርስቲያናዊ ድርጅትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ የሚሠራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ለዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመው ክርስቲያናዊ ድርጅት ሠራተኞች በተለያዩ ክልሎች ላይ የሠሩትን ጥናት እንደ መነሻነት በመጠቀም፣ የቤት ሠራተኞችና አሠሪዎች መብትና ግዴታቸው ምንድነው የሚለውን ጉዳይ ከተጠቃሚዎቹ በማወቅ የሕግ ማዕቀፍ የሚዘጋጅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት በተመለከተ ማንኛውም ዜጋ ወደ ውጭ ሥራውን ከጀመረበት ጀምሮ አገልግሎት እስከሚያገኝበት ድረስ፣ የራሱ የሆነ አሠራር እንዳለውና መመርያም ጭምር እንደተዘጋጀለት ጠቁመዋል፡፡

የቤት ሠራተኞች የሥራ ሁኔታቸው በሕግ ጥበቃ ባለመደረጉ እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰትና ልዩ ልዩ አካላዊ እንዲሁም ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማስቀረት በአሠሪና በሠራተኛ አዋጅ የተቀመጠውን ደንብ እንዲወጣ መንግሥትን እየወተወተ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ደንብ እስኪወጣ የሠራተኞቹን መብትና ግዴታ፣ እንዲሁም የአሠሪዎቹን ኃላፊነት የሚያሳይ የሥራ ውል ተነድፎ ሥራ ላይ እንዲውል መደረግ እንዳለበት ኢሠማኮ ያምናል ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት እንዲቻል ደንብና መመርያዎች እንዲወጡ በአዋጁ ቢደነገግም፣ በተፈለገው መጠን ተሠርቶ ባለመታየቱ እንደ ማንኛውም ሠራተኛ በጋራ በመሆን የጋራ ችግሮቻቸውን የሚመክሩበት፣ የመደራጀት መብት እንዲኖራቸው ያልተቋረጠ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አብራርተዋል፡፡

የቤት ውስጥ ሠራተኞች በአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ ተካተው ተገቢውንና ወጥ የሆነ አደረጃጀት እንዲኖራቸው ለማስቻል፣ የዓለም ሥራ ድርጅት ድንጋጌ ቁጥር 189 የኢትዮጵያ የሕግ አካል እንዲሆን ሁሉም ለባለድርሻ አካል የግሉን ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል፡፡

ኮንቬሽኑን ኢትዮጵያ እንድታፀድቅና የሕጎቿ አካል እንዲሆን ለማስቻል በሕጉ ላይ በቂ ዕውቀት ባላቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች አካላት በሚገኙ ባለሙያዎችን ጭምር በመጠቀም የሕግ አካላት፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የሠራተኞችና የአሠሪዎች አደረጃጀቶች፣ የፌዴራልና የክልል አስፈጻሚ አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የጋራ ውይይቶች አድርገው የተጎዱና የተረሱ ወገኖች ሰብዓዊና የሥራ ላይ መብቶቻቸው መጠበቅ እንዳለበት በማመን የጋራ ስምምነት ተደርሷል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...