Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአየር ንብረት ለውጥ ዋናው ችግር በዙሪያው የሚወጡ ፖሊሲዎች በየጊዜው መለዋወጥና ተግባራዊ አለመሆን...

በአየር ንብረት ለውጥ ዋናው ችግር በዙሪያው የሚወጡ ፖሊሲዎች በየጊዜው መለዋወጥና ተግባራዊ አለመሆን እንደሆነ ተነገረ

ቀን:

በተለያዩ ወቅቶች በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚወጡ ፖሊሲዎችና መመርያዎች ወደ መሬት ወርደው ተግባር ላይ አለመዋላቸው፣ በዘርፉ መሻሻል እንዳይኖር መሠረታዊ ችግር መሆኑ ተነገረ፡፡

ዳን ቸርች ኤድ (Dan Church Aid) የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ በሦስት የአፍሪካ አገሮችና በአንድ የኤዥያ አገር አደረግኩት ባለው ጥናት፣ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በየወቅቱ የሚወጡ ፖሊሲዎችና መመርያዎች ወደ መሬት ወርደው ተግባራዊ ባለመሆናቸው፣ የአየር ንብረት ለውጥ መባባስ መሠረታዊ ችግር መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

ድርጀቱ ‹‹ለሁለት ፈተናዎች አንድ መፍትሔ›› በሚል ከትናንት በስቲያ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ በኢትዮጵያ፣ በኬንያና በዑጋንዳ፣ እንዲሁም በኔፓል አገሮች በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን በጥናት አቅርቧል፡፡

ጥናታዊ ጽሑፉን ያቀረቡት በዳን ቸርች ኤድ የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ጥበቃ ኢነርጂ ቴክኒካል መሪ አቶ ኢልሚ ኑሪ ናቸው፡፡

አቶ ኢልሚ  እንዳሉት፣ የአየር ንብረት ለውጥ መባባስ አስመልክቶ የሚወጡ ፖሊሲዎች ተግባራዊ ካለመደረጋቸው ባሻገር፣ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረትና በቅንጅት ያለመሥራት ክፍተቶች በሁሉም የአፍሪካ አገሮች የታዩ መሠረታዊ ችግሮች ናቸው፡፡

ለአየር ንብረት ለውጥ የሚመደበው ገንዘብ ምን ያህል ለአካባቢ ጥበቃና ለልማት እየዋለ ነው የሚለው ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ መከታተል ያስፈልጋል ያሉት አቶ ኢልሚ፣    የተለያዩ አገሮችና ድርጅቶች ማኅበረሰቡን በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የባለቤትነትና አሳታፊነትን ሊያካትቱ ይገባል፡፡

ከጥናቱ ግኝት በመነሳትም አምስት የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተብለው ተቀምጠዋል፡፡ በቂ ገንዘብ መመደብ፣ ሁሉም አገሮች ተባብረውና ተጋግዘው በጋራ ለመሥራት መነሳሳት፣ የሚቋቋሙ ፕሮጀክቶች አካባቢያዊና ነባራዊ ሁኔታን መሠረት እንዲያደርጉ መከታተል፣ እንደ አገር ያሉትን መልካም ተሞክሮዎች ወደ አንድ በማምጣት ማጎልበትና ለሌሎች ማካፈል፣ እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የአየር ንብረት ለውጥ የሁሉም ጉዳይ መሆኑን ተረድተው በጋራ መሥራት የመፍትሔ ሐሳቦች ተብለው የተጠቀሱ ናቸው ፡፡

‹‹ጥናቱ የተካሄደባቸው ሦስቱ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ተመሳሳይ የአየር ንብረት ለውጥ ችግር የሚጋሩና ተመሳሳይ መፍትሔ የሚሹ አገሮች ናቸው፤›› ያሉት አቶ ኢልሚ፣ በሁሉም አገሮች የገንዘብ እጥረት፣ አብሮ የመሥራት ችግርና የፖሊሰ አለመተግበር በሦስቱም አገሮች የታዩ ችግሮች ናቸው፡፡

ፖሊሲ የሚያወጡ አካላት ያወጡትን ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲሆን ቢከታተሉ፣ አፈጻጸሙ ተቋማዊ እንዲሆን የሚወጡ ፖሊሲዎችን ማስፈጸም የሚያስችሉ ሕግና ደንቦች ወጥተው ቢሠሩ ፖሊሲው ተግባራዊ እንዲሆን ይረዳሉ የተባሉ ሐሳቦች ናቸው፡፡

‹‹ችግሩ የጥናትና የመረጃ እጥረት አይደለም›› ያሉት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አማካሪ የሆኑት አቶ አበራ እንዳሻው ናቸው፡፡ የበለፀጉ አገሮች በየወቅቱ ለታዳጊ አገሮች የሚገቡትን ቃል ተግባራዊ አለማድረጋቸው የመጀመሪያው ችግር ነው ያሉት አቶ አበራ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ስምምነቶችና የተኳኳሉ ንግግሮች ተግባራዊ ካልሆኑ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በታዳጊ አገሮች ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ከዚህ የከፋ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጎላ ችግር የማይፈጥሩ አገሮች በችግሩ አብረው እየታመሱ ነው ያሉት አማካሪው፣ በሚያስከትሉት ችግር በተለይ እንደ ምሥረቅ አፍሪካ ባሉ አገሮች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ አንበጣና ሌሎች ችግሮችን እያስከተለ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የችግሩ ጠንሳሽ አገሮች ችግሩን ልንቋቋምበት በምንችልበት ልክ ድጋፍ እያደረጉ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...