Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየእንስሳት በሽታን ለመከላከል የክትባት ምርትን በሦስት እጥፍ የሚያሳድግ ማቀነባበሪያ ላቦራቶሪ ሊገነባ ነው

የእንስሳት በሽታን ለመከላከል የክትባት ምርትን በሦስት እጥፍ የሚያሳድግ ማቀነባበሪያ ላቦራቶሪ ሊገነባ ነው

ቀን:

የአገር ውስጥ የእንስሳት በሽታ መከላከያ ክትባት ምርት በሦስት እጥፍ ለማሳደግና በዘርፉ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሟላ የማምረቻ ላብራቶሪ ማቀነባበሪያ ማዕከል ሊገነባ መሆኑን፣ ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ይህንን የገለጸው ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ‹‹ከእንስሳት ጤንነት እስከ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት›› በሚል መሪ ቃል፣ የ60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ የምሥረታ በዓሉን በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ቅጥር ግቢው ውስጥ ለማክበር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ታከለ ዓባይነህ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ኢንስቲትዩቱ የኢትዮጵያን የእንስሳት ሀብት ከተለያዩ የእንስሳት በሽታዎች ለመከላከል የሚያስችል ክትባትና መድኃኒቶችን በእጥፍ ለማምረት ደረጃውን የጠበቀ የማምረቻ ላብራቶሪ ማቀነባበሪያ ለመገንባት የአዋጪነት ጥናት እያካሄደ ነው፡፡

ኢንስቲትዩቱ በሰው ኃይልና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ከኢትዮጵያ አልፎ ወደ ተለያዩ አገሮች ምርቶቹን የሚልክ መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህ በፊት በዓመት አራት ሚሊዮን ክትባት የማምረት አቅሙን ወደ 300 ሚሊዮን በማሳደግ የአገር ውስጥ የእንስሳት ክትባት ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ መሸፈን መቻሉን አስረድተዋል፡፡

የላብራቶሪ ሕንፃ ግንባታው በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከናወን ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ በዓመት የክትባት አማካይ የማምረት አቅሙን ወደ አንድ ቢሊዮን ዶዝ ለማሳደግ ዕቅድ መያዙን ጠቁመዋል፡፡

በተለይ የእንስሳት ሀብት ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ፣ ከዚህ በፊት አራት ዓይነት የእንስሳት ክትባት ምርቶችን ወደ 23 ማሳደግ መቻሉን አክለው ገልጸዋል፡፡  

ከዚህ በፊት በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ አገሮች ከፍተኛ የእንስሳት ዕልቂት ያስከተለውን የደስታ በሽታ ለመቆጣጠር ኢንስቲትዩቱ መቋቋሙን ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅት የእንስሳት ሀብት ዘርፍን ከመደገፍ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

የክትባት ምርቱን ለአገር ውስጥ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ ለ33 አገሮች በመላክ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት መቻሉን፣ የኢንስቲትቱ የማርኬቲንግ ኃላፊ አቶ መስፍን ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በተለይ የኢንስቲትዩቱን ሎጎ በመጠቀም የዕብድ ውሻ መድኃኒት ከአገር ውስጥ አልፎ ለተለያዩ አገሮች በሕገወጥ መንገድ የሚሸጡ ግለሰቦች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

እንዲህ ዓይነት ችግሮች በኢንስቲትዩቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግር መፍጠሩን ጠቅሰው፣ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. በተዘጋጀው ክብረ በዓል የአርብቶና የአርሶ አደሩን ግንዛቤ በማሳደግ ዘርፉን ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የእንስሳት ሀብት ጤንነት በመጠበቅ ለአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻውን በመወጣት ዘርፉን ከተለያዩ ችግሮች እየታደገ መሆኑን፣ የመንግሥት የልማት ድርጅት ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለ ሚካኤል ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የእንስሳት ክትባትና መድኃኒት ጥራትን በማሳደግ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እያቀረበ የሚገኘውን የማምረት አቅም እንዲያሳድግ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግለት ገልጸዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...