Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ጽሑፍ ገልባጩ ባርትልቢ

ትኩስ ፅሁፎች

… ልማድ ይኾናል፤ ይጋባል አንዳንዴ የአንዳንድ ገጸ ባሕሪያት ንግግር። የባርትልቢ አንዱ ይመስለኛል ‹‹ባላደርገው እመርጣለኹ›› (I would prefer not to) ይላት አባባል።

ሣህለሥላሴ ብርሃነማርያም ከተረጐሟቸው ክላሲካል አጫጭር ልቦለዶች መካከል የኸርማን ሜልቪል (እ.ኤ.አ.1853) ‹‹ጽሑፍ ገልባጩ ባርትልቢ›› (Bartleby the Scrivener) አንዱ ነው። በታላቅ ድርሰትነቱ ላይ ጥያቄ የማይቀርብበት ይኽ አጭር ልቦለድ፣ ሲያነቡት ቀላል ግን ሲተረጉሙት ውስብስብ የሚኾን ዓይነት ነው።

ስም የለሹ ተራኪ የሚያስተዋውቀን ገጸ ባሕሪያት ለየት ያሉ ናቸው። ለሠላሳ ዓመታት በጥብቅና ያገለገለው ተራኪያችን፣ ይኽን ኹሉ ዓመት ሲያገለግል እንደ ባርትልቢ የተለየ ተቀጣሪ ሰው አጋጥሞት አያውቅም። ለዚያም ነው ስለርሱ ሲገልጥ ‹the strangest I ever saw, or heard of› የሚለን።

እዚያ ቢሮው የምናገኛቸው ተቀጣሪዎቹ አንዱ ጠዋት ብስጩ ሲኾን፣ ኹለተኛው ወደማታ የሚናደድ ነው። ሦስተኛው እንኳ የሚላላካቸው የ12 ዓመት ጩጬ ነው። የተናዳጆቹን ሰዓት ጠብቆ የሚታይባቸው የባሕሪ ለውጥ ብዙም ለተራኪው የሚገርመው ያልኾነው፣ የባርትልቢ ከዚያም በላይ ስለኾነ ነው። ለጥቂት ቀናት በጣም በአሪፉ ሲሠራ የነበረ ሰው፣ ሲታዘዝ ድንገት ‹‹ባላደርገው እመርጣለኹ›› ማለት ይጀምራል። ከዚያ ጨርሶ ሥራ መሥራትም፣ መንቀሳቀስም እምቢ ይላል። ምግብ እምብዛም ሲመገብ የማይታየው ባርትልቢ፣ ከቢሮም ሲንቀሳቀስ አይታይም።

አሠሪው አንድ እሑድ ከቤተስኪያን መልስ ወደ ቢሮው ጎራ ቢል ያጋጠመው ግን የተለየ ነው። የራሱን ቢሮ በቁልፉ መክፈት ያቅተዋል። ከዚያ በሩ ከውስጥ ይከፈታል። ባርትልቢ እሑድም ከቢሮ አልወጣም። አለባበሱም የእሑድ ዓይነት ነው። አሠሪው ሊገባ መፈለጉን ስላወቀ፣ አሠሪው ጥቂት አካባቢው ላይ ተንጎራድዶ እንዲመለስ ይጠይቀዋል። አሠሪው ሲመለስ ቁልፉ ሳያስቸግረው ከፍቶ ሲገባ ማንም የለም። በደንብ ቢሮውን ሲቃኝ፤ ላልታወቀ ጊዜ ያህል ባርትልቢ ቢሮው ውስጥ ሲበላ፣ ሲለብስና፣ ሲያድር እንደነበር ይገነዘባል። (ብርድልብስ ኹሉ ያገኛል)። ከዚያ እንዲኽ ይላል፦ ‹‹Yes, thought I, it is evident enough that Bartleby has been making his home here, keeping bachelor’s hall all by himself.” (አዎ ቢሮውን ቤቱ አድርጎታል)።

ባርትልቢ መሥራት ካቆመ በኋላ እንኳ፣ አሠሪው ተጨማሪ የኪስ ገንዘብ ሰጥቶ ከሥራው እንዲለቅ ቢፈልግም ባርትልቢ እምቢ ባይ ኾነ። አሠሪው ቢሮውን ቀይሮ ለቆ ቢወጣም የባርትልቢ ነገር እስከመጨረሻው አይለቀውም። በኋላ ላይ የተቸገሩ አዳዲስ የቢሮው ተከራዮች በጉልበት ሲያስወጡት የቢሮው ደረጃ ላይ ተቀምጦ አልለቅ ስላለ ለፖሊስ አመልክተው በቤት አልባነት (vagrant ተብሎ) ይታሰራል።

ወዘተ…….

ሲያልቅ ተራኪው ይኽን ይላል (ተሰንቅሮ የሚቀር ዓረፍተ ነገር)፦ “Ah, Bartleby! Ah, humanity!”

– ፀደይ ወንድሙ በማኅበራዊ ትስስር ገጿ እንደከተበችው

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች