Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ንግድ ባንክና መቻልን ለዋንጫ ያፋጠጠው ፕሪሚየር ሊጉ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና መቻልን ለዋንጫ ያፋጠጠው ፕሪሚየር ሊጉ

ቀን:

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ ፍጻሜውን ሊያገኝ የሁለት ሳምንት ጨዋታ ብቻ ቀርቶታል፡፡ ለፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮንነት እንግዳ የሆኑት ንግድ ባንክና መቻል፣ በአንድ ነጥብ ልዩነት የሊጉን የደረጃ ሠንጠረዥ አንደኛና ሁለተኛ በመሆን ቀጣዮቹን ጨዋታዎች በጉጉት ይጠብቃሉ፡፡

በዚህም ምክንያት ለፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ቅርብ የሆኑት ሁለቱ ክለቦች አወዳዳሪው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር፣ በተለይም ከጨዋታ ማጭበርበር ጋር የተያያዙ ክፍተቶች እንዳይፈጠሩ ልዩ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚጠበቅበት በየበኩላቸው ሥጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

በዘንድሮ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጣበት ዓመት የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ሁለት የጨዋታ መርሐ ግብር ቀርቶታል፡፡ ዓምና ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የመጣው መቻልም የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በተለይም ለቡድኑ ለ80ኛ ዓመት ክብረ በዓሉ ለማበርከት በእጅጉ እንደሚፈልገው ይናገራል፡፡

ከዚህም የተነሳ ይመስላል የሁለቱ ክለቦች ቀጣይ ተጋጣሚዎች በሜዳ ላይ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ከወዲሁ ማነጋገር ጀምረዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በ29ኛው ሳምንት ጨዋታ የሚገጥመው፣ የመውረድ ሥጋት ካለበት ሻሸመኔ ከተማ ጋር ከመሆኑ አኳያ፣ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም የሚሉ አሉ፡፡

በዚያው ልክ የመቻል ተጋጣሚም አዳማ ከተማ ለዋንጫውም ሆነ ለወራጅ ቀጣናው ዕድልም ሆነ ሥጋት የሌለበት መሆኑ፣ የጨዋታውን ሚዛን እንዳያስተው ሥጋት መሆኑ እንዳልቀረም በተመሳሳይ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

ሁለቱ የዋንጫ ተፎካካሪዎች በ30ኛው ሳምንትና የሚጫወቱት የመውረድ ሥጋት ከሌለባቸው ክለቦች ጋር ነው፡፡ ንግድ ባንክ ከመድን መቻል ከድሬዳዋ ጋር የሚያደርጉት ግጥሚያ ከወዲሁ አጓጊ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...