Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በአዲስ አበባ እየተከናወነ ይገኛል

የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በአዲስ አበባ እየተከናወነ ይገኛል

ቀን:

ዓመታዊው የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ከተማ ከሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡ በሻምፒዮናው አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ ስምንት ክልሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን በውድድሩ ዋዜማ በሰጠው መግለጫ፣ ሻምፒዮናው እስከ 23 ቀን ድረስ በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች እንደሚከናወን አስታውቋል፡፡

የመክፈቻውን ውድድር በአዲሱ የቦሌ ቡልቡላ መንገድ አድርጎ የማጠቃለያ ውድድሩን ደግሞ ዓድዋ መታሰቢያ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ይፍሩ ተናግረዋል፡፡

በሻምፒዮናው እየተሳተፉ የሚገኙት ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ሲዳማ እንዲሁም በቅርቡ ወደ ክልልነት የመጡት፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ በውድድሩ አራት የግል ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 136 ብስክሌተኞች እንደሚወዳደሩ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድሙ ኃይሉ አብራርተዋል፡፡

ሻምፒዮናው ተተኪ ስፖርተኞች የሚፈጠሩበትና የሚመረጡበት፣ በዓለም የብስክሌት ኅብረት (ዩሲአይ) የመረጃ ማዕከል የሚመዘገቡበት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡  

እንደ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ከሆነ፣ በዚህ ውድድር ጥሩ ሰዓት የሚያስመዘግቡ ተወዳዳሪዎች ከዓለምና አኅጉር ተሳትፎ በተጨማሪ፣ በቱር ደ ፍራንስ ቱር ሩዋንዳና ቱር ጋቦን በመሳሰሉት ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ዕድል ይፈጥርላቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...