Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለመጪው በጀት ዓመት ከፍተኛ መጠባበቂያ በጀት መቅረቡ በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ

ለመጪው በጀት ዓመት ከፍተኛ መጠባበቂያ በጀት መቅረቡ በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ

ቀን:

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚጀመረው የ2017 በጀት ዓመት ያቀረበው የመጠባበቂያ በጀት፣ ካለፈው ዓመት ከእጥፍ በላይ ያደረገው ምን የተለየ ሥጋት ስላለ ነው በማለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ አስነሳ፡፡

ለ2017 በጀት ዓመት ከተረቀቀው 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ 81.4 ቢሊዮን ብር በመጠባበቂያነት መደልደሉ ነው ጥያቄ ያነስነሳው፡፡

በረቂቅ በጀቱ ላይ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ የሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከትናንት በስቲያ ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም.  ከገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በረቂቅ በጀቱ ላይ ውይይት አድርጎ ነበር፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የበጀት ረቂቁን በተመለከተ መልስ ያሻቸዋል ያላቸውን ጥያቄዎች ለገንዘብ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች አቅርቧል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በዚህም ለመጪው ዓመት የቀረበው 81.4 ቢሊዮን ብር መጠባበቂያ ለ2016 ዓ.ም. ተመድቦ ከነበረው 34.1 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር፣ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ጠቅሶ፣ በዚህ ልክ ሊጨምር የቻለው ምን የተለየ ሥጋትን ታሳቢ በማድረግ ነው በማለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተጨማሪ በጀት ለተቋማት ሲፈቀድ ፍትኃዊነቱ በምን ይረጋገጣል? ከፍ ያለ መጠባበቂያ መያዝ ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ሥራዎቻቸውን በዕቅድ እንዳይመሩ አሉታዊ ተፅዕኖ አይኖረውም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ለመጠባበቂያ የያዝነው በጀት ከሌላው ጊዜ አንፃር ከፍ ያለ መሆኑ ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ለተቋማት የሚደረግ ተጨማሪ በጀት አይደለም፤›› ብለዋል።

መንግሥት በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ያልታሰቡ አስቸኳይ አገራዊ ጉዳዮች ከፍ ያለ መጠባበቂያ በጀት መያዝ ያስፈልጋል በሚል ታሳቢነት ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

 ለ2017 ዓ.ም. በቀረበው በጀት ‹‹ከተቋማት ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ እንዳይመጣ ዝርዝር ውይይት ተደርጎበትና መግባባት ላይ ተደርሶ አቅጣጫ ተቀምጧል፤›› ያሉት ሚኒስትር  ደኤታው፣  በተለይ ዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ተደጋግሞ በሚነሳ የደመወዝና የካፒታል በጀት ጥያቄ በማያዳግም መንገድ መልስ ለመስጠት ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም ተቋማት የሚያስፈልጋቸውን በጀት አቅርበው እንዲካተት መደረጉን አክለዋል፡፡

በተመሳሳይ የገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ተፈሪ ደመቀ በሰጡት አስተያየት፣  የ2017 ዓ.ም. በጀት ድልድል ገንዘብ አጠረኝ ማለት የማይቻልበትና ከተቋማት ጥያቄ እንዳይመጣ ተደርጎ መደልደሉን ገልጸዋል፡፡  ተቋማት በመደበኛ በጀት ዓመቱን ሙሉ ሥራቸውን ለማከናወን እንዲችሉ መደልደሉን፣ በተመሳሳይ የካፒታል በጀትም የተመደበው በዚያው ልክ  ከሥራ ዕቅድ ጋር በማጣጣም  እንዲያከናውኑ ለማስቻል ነው ብለዋል።

ለሁሉም ተቋማት የበጀት ጭማሪ በመደረጉ የተደለደው በጀት ቅሬታ የሚቀርብበት  አለመሆኑን ገልጸው፣ በደመወዝ ረገድም ቢሆን ታሳቢ ተደርጎ መመደቡን አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...