Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትላቸው የሥራ መልቀቂያ አስገቡ

የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትላቸው የሥራ መልቀቂያ አስገቡ

ቀን:

የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የሥራ መልቀቂያ አስገቡ።

ሪፖርተር ያገኘው የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ እንደሚያሳየው፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ፀጋይ ብርሃነ ገብረተኸለ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ገብረ አምላክ የዕብዮ በላይ በገዛ ፈቃዳቸው የሥራ መልቀቂያ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ማስገባታቸውን ይገልጻል።

 ከዘጠኝ ወራት በፊት ባላቸው ሙያ የተሰጣቸውን የሕዝብና የመንግሥት ኃላፊነት ተቀብለው፣ ህልውናው ከባድ አደጋ ላይ የወደቀውን የፍትሕ ሥርዓት ለማሻሻልና የተለያዩ ተቋማዊ የማሻሻያ ዕርምጃዎችን ሲወስዱ መቆየታቸውን በደብዳቤው ገልጸዋል።

‹‹በክልላችን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራር ሆነን የመሥራት ዕድሉን በማግኘታችን አክብሮት አለን፡፡ ሆኖም ቆይታችን አጭር ቢሆንም ይህንን ከባድ ኃላፊነትና ተልዕኮ ይዘን በአመራርነት መቀጠልና በጀመርነው አቅጣጫ ለውጥ ለማምጣት ዕድል ማግኘት አልቻልንም፡፡ ስለዚህ በውስጥ አጠቃላይ በአስተዳደር፣ በፍትሕ ሥርዓቱና በፍትሕ አካላት የሚያጋጥሙንን ፈተናዎችና እንቅፋቶች ለመቀነስ ኃላፊነታችንን ለመወጣት ስላልቻልን፣ በሌሎች መንገዶች መርዳት እንደምንችል እርግጠኞች ስለሆንን፣ በቅንነት ሥልጣን ለመልቀቅ መወሰናችንን በትህትና እናሳውቃለን፤›› የሚል ደብዳቤ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አስገብተዋል።

‹‹ከክልላችን ውስጣዊ ችግሮች አኳያ በታማኝነት በየፍርድ ቤቶቻችን ተገኝተን ከጥፋት የተረፉት ወገኖቻችን ፍትሕ እንዲያገኙ ማድረግና ማገልገል ከታሪክ አኳያ የእያንዳንዱን ዜጋ ተነሳሽነትና ትግል የሚጠይቅ ልዩ ሥራ ሲሆን፣ መልቀቂያችን ተቀባይነት እስኪያገኝ ድረስ ሕዝባዊ ኃላፊነታችንን መወጣት እንቀጥላለን፤›› ሲሉ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።

 ሪፖርተር የኃላፊነት መልቀቂያ ያስገቡትን ኃላፊዎች ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቢቀርም፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጮች የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን በማረጋገጥ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ መልቀቂያቸውን እስካልተቀበሉ ድረስ በሥራቸው ላይ መቆየት ግዴታቸው ነው ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...