Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየክህሎት ልማትን የሚጠይቀው አረንጓዴ ኢኮኖሚ

የክህሎት ልማትን የሚጠይቀው አረንጓዴ ኢኮኖሚ

ቀን:

ኢትዮጵያ በአሥር ዓመታት ውስጥ ለመተግበር ከያዘችው ዕቅድ ውስጥ በመተግበር ላይ የሚገኘው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አንዱ ነው፡፡ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ የወጣ ቢሆንም ወደ መሬት አውርዶ ለመተግበር የግንዛቤ ጉድለትና ሌሎች ችግሮች ፈተና መሆናቸው አልቀረም፡፡

ፈተናዎቹን ቀርፎ የአረንÕዴ ኢኮኖሚ ልማት እውን ይሆን ዘንድ የሰው ኃይል ልማት ዝግጅቱ የክህሎት ልማት አቅጣጫን የተከተለ መሆን እንዳለበት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋም ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ይገልጻሉ፡፡

ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ተግዳሮት የሆነውን የሰው ሀብት ልማት እጥረትና  ሌሎች ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ተቋሙ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ባዘጋጀው የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ንግግር ያደረጉት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ለቀጣዮቹ አሥር ዓመታት  አገሪቱ  የምትጓዝበት የአረንÕዴ ኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚፈጸመው፣ የሰው ሀብት ልማት ላይ  ትኩረት ተሰጥቶ ከተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

‹‹አረንÕዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ከተፈለገ ሰው ላይ ሊሠራ ይገባል›› የሚሉት ብሩክ (ዶ/ር)፣ በቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተkማት በኩል የሚያልፉ ሠልጣኞች ስለ አረንÕዴ ልማት የተሻለ ዕውቀት ይኖራቸው ዘንድ የአረንጓዴ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና›› በሚል ለሁሉም የቴክኒክና ሙያ ሠልጣኝ ተማሪዎች ሥልጠናዎችን ለመስጠት እንቅስቃሴ  ላይ ስለመሆናቸው አክለዋል፡፡

የግብርና፣ የግንባታና ሌሎች ዘርፎች አረንጓዴ ኢኮኖሚን በተከተለ የሰው ሀብት ልማት ዙሪያ አተኩረው ሊሠሩ እንደሚገባ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የነዳጅ ተሽከርካሪዎች ወደ ኤሌክትሪክ እየተቀየሩ መሆናቸው ለአረንÕዴ ልማት ጅማሮ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ 

በቱሪዝም ልማቱ፣ በግንባታ ዘርፍና በመሰል ተkማት አረንÕዴ ልማትን  በስፋት ለመተግበር የሰው ኃይል ዝግጅቱ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ፣ ችግሩን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል ዝግጅት ሊደረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ ዘርፎች የሚሳተፉ አካላት የአረንጓዴ ልማት አቅጣጫን የሚከተሉ ሊሆን ይገባል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሠልጣኞችም የአረንÕዴ ልማት   አቅጣጫን በተከተለ መልኩ ሥልጠናውን መውሰድ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

የአገሪቱ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ አረንጓዴ ኢኮኖሚ  ልማት ነው ከተባለ የሰው ኃይል ዝግጅቱ ይህንኑ የተከተለ ሊሆን እንደሚገባና አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ችግኝ መትከል ብቻ መሆን እንደሌለበትም ተናግረዋል፡፡

‹‹የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ችግኝ በመትከልና በሌሎች ቁንፅል ሐሳቦች የሚገለጽ አይደለም›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፍ  የሚመለከት ስለመሆኑ  አውስተዋል፡፡

እንደ ብሩክ (ዶ/ር)፣ የአረንጓዴ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አቅጣጫን ተከትሎ ተግባራዊ ማድረግ የብዙዎች ሚና መሆን አለበት፡፡ የፖሊሲ አቅጣጫን ስትራቴጂን ማሳየት፣ የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ግንዛቤ ማስጨበጥና የማስተባበር የመንግሥት ሚና ሊሆን ይገባል፡፡

ሌሎች አጋር አካላትም የሰው ሀብት ልማት ላይ ሊሠሩ ይገባል፡፡ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት መነሻ ፖሊሲዎችም በደንብ ሊብራሩና ተጨባጭ ወደሆነ ተግባር ሊቀየሩ ይገባል፡፡

በተጀመረው የአረንጓዴ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና መንግሥት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን  ሊያስቀጥሉ የሚችሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን ማፅደቁ እንደ መልካም ዕድል መሆኑን፣ የጠቀሱት ብሩክ (ዶ/ር) በሚመለከታቸው አካላት መካከል ያለው ቅንጅትና ተናቦ መሥራት  በሚፈለገው ልክ አለመሆን ደግሞ ተግዳሮት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ 2,300 የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት ሲኖሩ፣ በተቋማቱ የአረንጓዴ ቴክኒክና ሙያ ክበቦች ተቋቁመው ግንዛቤ እንዲፈጠር የማድረግ ሥራ ተጀምሯል፡፡ ጅምር ጥረቶቹ ከሰፉ ከተጠናከሩ፣ ከቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተkማት የሚወጡ ወጣቶች ስለ አረንÕዴ ኢኮኖሚ የተሻለ ዕውቀትን ይዘው እንደሚወጡም ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...