Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅጎጃም ሳይመታ

ጎጃም ሳይመታ

ቀን:

አለቃ ገብረሐና… አንዲት መልከ መልካም ሴት መኖሪያ ቤቷ ቀጠሮ ይዘው ኖሮ በሰዓታቸው ሲደርሱ ሴትዮዋ በሩን ገርበብ አድርጋ እሳቸውን ስትጠብቅ ቆይታ እንቅልፍ በዚያው ይዟት ሄዷል፡፡ አለቃ ገርበብ ያለውን በር ትንሽ ገፋ አድርገው ሲገቡ #እሜቲቱ$ ተኝታለች፡፡ አለቃ ከመደቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ወዲያው አንድ #የባዕድ$ ድምጽ ይሰማል ከስር፡፡ ብም …

#ትግራይን ምታ…$ አለች ሴትዮዋ፡፡ በእንቅልፍ ልቧ ነው፡፡ አለቃ #ፈገግ$ አሉና ተከታዩን ድምጽ ይጠባበቃሉ፡፡ አሁንም #ብም$ አለ፡፡

#ጐንደርን…$ ምታ አለች፡፡ አለቃ ሳቃቸውን በግድ አፍነው ይዘው… #እነዘ ይሴለሱ$ እያሉ አሁንም በልባቸው ቀጣዩን ይጠብቃሉ፡፡

#ብም$ አለ፡፡ እንደተለመደው

#ጐጃምን ምታ$ ብላ ከመቅጽበት ከእንቅልፏ ነቃች አለቃ መደብ ላይ ቁጭ ብለዋል፡፡

#ውይ… አፈር በሆንኩት አለቃ ቆዩ እንዴ ከመጡ… አለች$ የፊቷን ላብ በሸማዋ እየጠረገች እንደ ማፈርም እንደ መደነቅም እያለች፡፡

#አዎ…$ አሉ አለቃ፡፡ #ከመጣሁማ ቆየሁ ገና ጎጃም ሳይመታ ነው የመጣሁት…$ ሲሏት #ኡኡቴ…$ አለችና ወደ ሌላ ወጋቸው ተሸጋገሩ፡፡

– ንጉሤ አክሊሉ ‹‹ለኢትዮጵያ ታሪኳ – ነው መልኳ›› (2001)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...