Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየፈላስፎቹ ድምፅ በአንጋረ ፈላስፋ

የፈላስፎቹ ድምፅ በአንጋረ ፈላስፋ

ቀን:

የሁለት ሺሕ ዓመታት የዘለቀው የግእዝ ሥነ ጽሑፍ በጉያው ከያዛቸው መካከል ፍልስፍናዊ ጽሑፎች ይገኛሉ፡፡ ከግሪክ ሆነ ከዓረቢኛ ወደ ግእዝ ከተተረጎሙት አንዱ የፈላስፎችን ንግግሮች የያዘው ‹‹አንጋረ ፈላስፋ›› ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ በደብረ ቢዘን ገዳም ያገኙት ሊቀ መዘምራን ሞገስ እቁበ ጊዮርጊስ ከግእዝ ወደ አማርኛ ተርጉመውት በ1950ዎቹ መገባደጃ የኅትመት ብርሃን አይቷል፡፡ በተደጋጋሚም ታትሟል፡፡ እሳቸው ካረፉ በኋላ ከግእዝ ወደ ትግርኛ ተተርጉሞ በአስመራ ከተማ ታትሞ ተሠራጭቷል፡፡

፩. አንዱን ሰው ማን ገሠፀህ ብለው ጠየቁት፡፡ እሱም መልሶ የሰነፎችን ስንፍና

  አይቼ ራቅሁ ከዚህም የተነሳ ተገሠፅኩ አለ፡፡  

፪. ዲዮጋንስ አንድ ሰነፍ ሰው በደንጊያ ላይ ተቀምጦ አየና፣ ደንጊያው በደንጊያ ላይ

  ተቀምጧል አለ፡፡

፫. አፍላጦንን ሰው ጠላቱን በምን መንገድ ሊበቀለው ይችላል ብለው ጠየቁት፡፡ እሱም አብዝቶ ጥሩ ነገር ያደረጉለት እንደሆነ ነው ብሎ መለሰ፡፡

   ፬. ከጠቢባን አንዱን እንዲህ ብለው ጠየቁት፣ የሚጠቅምና የሚያስተክዝ ሥራ

     ምንድነው፡፡ እሱም የክፉ ሰዎች ሞት ነው ብሎ መለሰ፡፡

፭.ዲዮጋንስን ሞት እንዴት ናት ብለው ጠየቁት፡፡ እሱም ሀብታሞችን የምታስደነግጥ በድሆች ዘንድ ግን የምትፈለግ ናት አላቸው፡፡

፮. ዲዮጋንስ አንድ መልከ መልካም ሰው ሲዋሽ አየው፤ እሱም ቤቱ ያማረ ሆኖ የሚኖርበት ግን ክፉ ነው አለ፡፡

፯. አንድ አዋቂ ወደ ሌላ አዋቂ መኖሪያ ሄዶ እንዲህ ብሎ ጠየቀው፡፡ ብቻህን ስትኖር እንዴት አይሰለችህም አለው፡፡

እሱም መልሶ እንዲህ አለው፡፡ እኔ እኮ ብቻዬን አይደለሁም፡፡ ከብዙ አዋቂ ሰዎች ጋር ነኝ፣ ከእነሱም ጋር እነጋገራለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ እጁን ዘርግቶ ካጠገቡ ብዙ መጻሕፍት አወጣና ይህ ጋሊኖስ ሕያው ነው፡፡ አብቅራጥም ይገስፃል፡፡ ሶቅራጥም ያስተምራል፡፡ አፍላጦንም ይናገራል፡፡ አርስጣጣሊስ ምሳሌ ይመስላል፡፡ ሕርምስም ምላሽ ይሰጣል፡፡ ፎርፎርዬስ ይመክራል፡፡ ጐርጐርዮስ ይናገራል፡፡  ከእነዚህ ሁሉ መካከል ከፈለግኩት ከእኔ ጋር ይጫወታል አለው፡፡

– አንጋረ ፈላስፋ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...