Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርት ሰማንያኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው የመቻል ስፖርት ክለብ

 ሰማንያኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው የመቻል ስፖርት ክለብ

ቀን:

‹‹ጦር ሠራዊት›› በሚለው መጠሪያ በ1936 ዓ.ም. የተመሠረተው የመቻል ስፖርት ክለብ፣ የቀድሞ ክብርና ዝናውን ለመመለስና ለማጠናከር ዜጎች ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡

 ሰማንያኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው የመቻል ስፖርት ክለብ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን
ፎቶ መቻል ስፖርት ክለብ

‹‹መቻል ለኢትዮጵያ›› በሚል መሪ ቃል ለአንድ ወር የሚቆይ የዝግጅት መርሐ ግብር እየተከናወነ እንደሚገኝ የክለቡ የቦርድ አመራሮች ገልጸዋል፡፡

የአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመቻል ስፖርት ክለብን 80ኛ የምሥረታ ክብረ በዓልን አስመልክቶ፣ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የውይይት መድረክ፣ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ሕዝባዊ መሠረት ያለው የመቻል ስፖርት ክለብን ለማጠናከር እየተደረገ ባለው ጥረት ዜጎች ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው፣ የመከላከያ ሥነ ልቦና ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን መናገራቸው ተገልጿል፡፡

መቻል በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ትልቅ አሻራ ያለው እንደሆነ፣ ክለቡ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር የተሳሰረ ስለመሆኑ ጭምር በውይይቱ ታዳሚዎች ተነግሯል፡፡

የመቻል ስፖርት ክለብ የሥራ አሠራር ቦርድ ሰብሳቢ ሰይፈ ጌታሁን (ዶ/ር)፣ ከሰባት ወራት በፊት የተቋቋመው ቦርድ በውስጡ በንግዱ ዘርፍ ያሉ ባለሀብቶችና ታዋቂ ግለሰቦችን ማካተቱን፣ ዋና ዓላማውም የመቻል ስፖርት ክለብ ዘመናዊ ቁመና ይኖረው ዘንድ የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎችን ማከናወን እንደሆነ ተናግረዋል፡፡  

ክለቡ የራሱ የገቢ ምንጭ እንዲኖርው በማድረግ በዘላቂነት እንዲደገፍ ቦርዱና የሚመለከታቸው አካላት ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ፣ ለዚህም የስፖንሰርሽፕ ስምምነቶች ለማድረግ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ ስለመሆናቸው ጭምር ተነግሯል፡፡

የክለቡ የቀድሞ ተጫዋቾችና አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀንን ጨምሮ በታደሙበት የውይይት መድረክ፣ የመቻል ስፖርት ክለብ ከምሥረታው አንስቶ ለኢትዮጵያ ስፖርት ዕድገት የማይተካ ሚና ያበረከተና አሁንም እያበረከተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የመቻል ስፖርት ክለብ ከእግር ኳስ በተጨማሪ በአትሌቲክሱ የኢትዮጵያን ስምና ዝና ከፍ በማድረግ ትልቅ ሥራ የሠሩ አትሌቶችን ያፈራ መሆኑን በተመለከተም፣ አንጋፋዎቹ ሻምበል እሸቱ ቱራና ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ የክለቡን ታሪካዊነት በመጥቀስ፣ ክለቡ ክብሩንና ዝናውን አስጠብቆ እንዲቀጥል እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ በእጅጉ እንደተደሰቱ መናገራቸው ታውቋል፡፡

የመቻል 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ዝግጅቶች መካከል፣ የፓናል ውይይቶች፣ የጎዳና ላይ ሩጫዎች፣ የስፖርታዊ ውድድሮች፣ እንዲሁም ከውጭ አገር እግር ኳስ ቡድን ጋር የሚደረግ የወዳጅነት ጨዋታዎች ይገኙበታል፡፡ የመቻልን ስምንት አሠርታት ጉዞ የሚዘክር ዘጋቢ ፊልም ለሕዝብ ዕይታ ይቀርባል፡፡  

በዝግጅቱ ገቢ ማሰባሰብ ብቻ ሳይሆን መቻል ቀጣይነት ያለው፣ ራሱን በራሱ የሚመራና ሕዝብና ሠራዊቱ የሚኮሩበት ስፖርት ክለብ የማድረግ ሥራዎች እንደሚከናወኑ በውይይቱ ተነግሯል፡፡ ክለቡ ከዚህም ባሻገር በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ ምርጥ 10 ቡድኖች መካከል አንዱ እንዲሆን እየተሠራ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡

የመቻል ስፖርት ክለብን ለማጠናከር እየተደረገ ባለው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ ሼህ መሐመድ አል አሙዲ፣ አቶ በላይነህ ክንዴና ሌሎችም ባለሀብቶች በከፍተኛ ደረጃ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ነው የተነገረው፡፡ የመቻል 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ይቀጥላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...