Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለጨርቃ ጨርቅና ለአልባሳት ሠራተኞች የመደራጀትና ምቹ የሥራ ከባቢ ለመፍጠር ጥናት ሊደረግ ነው

ለጨርቃ ጨርቅና ለአልባሳት ሠራተኞች የመደራጀትና ምቹ የሥራ ከባቢ ለመፍጠር ጥናት ሊደረግ ነው

ቀን:

የጨርቃ ጨርቅና የአልባሳት ኢንዱስትሪ ሠራተኞችን የመደራጀትና ምቹ የሥራ ከባቢን ለመፍጠር ያሉትን ክፍተቶች ለመፈተሽ ጥናት ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን፣ ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) አስታወቀ፡፡

ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) ይህንን የገለጸው ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጉዳዩን በተመለከተ መነሻ ሐሳብ ለመሰብሰብ፣ ከግልና ከመንግሥት ተቋማት ከተውጣጡ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሲያደርግ ነው፡፡

የፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ የምርምርና የኅትመት ክፍያ አስተባባሪ ኢዛና ዓምደወርቅ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ምቹ የሥራ ከባቢ ከሌላቸው የሥራ መስኮች ውስጥ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ አንዱ ነው፡፡

‹‹ከዚህ ቀደም የፋብሪካ የሥራ ኃላፊዎችን አነጋግረን የሠራነው ጥናት እንደሚያሳየው፣ አሠሪዎች በሳምንት ውስጥ ብዙ ጊዜያቸውን የሚሳልፉት አዳዲስ ሠራተኞችን ለመመልመል በሚያደርጉት ጥረት መሆኑን ለማየት ችለናል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ይህ ድርጊት አንድ ሠራተኛ ተረጋግቶ እንዳይሠራ ከማድረጉም በላይ፣ አሠሪው ከሠራተኛው የሚፈልገውን እንዳያገኝ ያደርገዋል፤›› ያሉት አስተባባሪው፣ በአጠቃላይ በዘርፉ ላይ ያሉትን ችግሮች ለማየትና ለመፈተሽ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎበት ጥናት እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡  

 በኢትዮጵያ የአሠሪዎችም ሆነ የሠራተኞች የመደራጀት ሁኔታ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ጠቅሰው፣ የእነዚህን ሁለት ጉዳዮች ጥቅምና ጉዳታቸው ምንድነው የሚለውን በጥናት በማስደገፍ ወደፊት የፖሊሲ አቅጣጫ ለማስያዝ የሚረዳ መሆኑን አክለዋል፡፡

ጥናቱ ሠራተኛው፣ አሠሪውም ሆነ መንግሥት የሚሳተፉበት መሆኑንና ዘርፉም በመረጃ የተደገፈ እንዲሆን የተለያዩ መረጃዎች ይሰብስቡ ብለዋል፡፡

‹‹በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ከሚይዙ ጉዳዮች መካከል የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ አንዱ ነው፤›› ያሉት የፕሮጀክቱ ተመራማሪ ናቸው፡፡

በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ውስጥ ምን የተሠራ ነገር አለ? ምንስ የጎደሉ ነገሮች አሉ? የሚሉትን ቢያንስ በምን ዓይነት መንገድ ማሻሻል ይቻላል የሚሉ ጉዳዮችን ለፖሊሲ ግብዓትነት ለመጠቀም ጥናት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ጥናቱም ለሁለት ዓመታት ያህል እንደሚቆይ ገልጸው፣ የሚመለከታቸው አካላት በዚህ ላይ ያላቸውን ሐሳብ በግብዓትነት እንዲያቀርቡ ውይይት የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢንዱስትሪዎች ምቹ የሥራ አካባቢ መፍጠር ከቻሉ፣ መንግሥትም ሆነ አሠሪዎች ከፈለጉበት ግብ መድረስ እንደሚችሉና ዘርፉም ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያድግ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...