Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአስጊው የቲቢ በሽታ አሁናዊ ገጽታና መፍትሔው

አስጊው የቲቢ በሽታ አሁናዊ ገጽታና መፍትሔው

ቀን:

የቲቢ (ሳንባ ነቀርሳ) በሽታ ትልቁ የዓለም የጤና ፈተና ሆኖ መቀጠሉ በየጊዜው የሚነገር ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ በተደረጉ ጥናቶች እንደተገመተው ቲቢ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ይጎዳል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በ2023 ባወጣው ሪፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ 10.6 ሚሊዮን ሰዎች በቲቢ እንደተጠቁና ከእነዚህ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን ሕይወታቸው  እንደጠፋ ገልጿል፡፡

የቲቢ በሽታን በቀላሉ መከላከል እየተቻለ አምራች ወጣቶችን፣ ታዳጊዎችን እናቶችንና አዛውንቶችን በሞት ይነጥቃል፡፡  ይህ ደግሞ  በኑሮ ውድነት፣ በድርቅና በእርስ በርስ ጦርነት እየተፈተነች ላለች አገር ፈታኝ ነው፡፡

 ቲቢን ጨምሮ በኤችአይቪ ኤድስና በሌሎች ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች በየዓመቱ የሚሞቱ ወገኖች ቁጥር እያሻቀበ ስለመሆኑ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጀት (ዩኤስኤአይዲ) ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጥራቱን የጠበቀ የቲቢ ምርመራ አለመኖርና  ውስንነት እንዲሁም የተሟላና ዘመናዊ  የሕክምና መመርመሪያ መሣሪያ እጥረት የግንዛቤ ጉድለት የሚሉትና ሌሎች ምክንያቶች የበሽታው ሥርጭት እንዲጨምር ከሚያደርጉት መካከል በዋናነት ተጠቅሰዋል፡፡

የቲቢ በሽታን በመለየትና በማከም መሻሻል ቢታይም በበሽታው የተጠቁትን ሁሉ ፈልጎ ማግኘትና ሕክምናውን እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ዛሬም ትልቅ ከፍተት ሆኖ ስለመቀጠሉ የሚያትተው ሪፖርቱ፣ በአሁኑ ወቅት የቲቢ ሕሙማን በጤና ተቋም ሕክምና እየተደረገላቸው ቢሆንም ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ሕክምና ያልጀመሩ እንዳሉም ተጠቅgል፡፡

በሽታው እንዳለባቸው የሚጠረጠሩና ተመርምረው ሕክምናቸውን ያልጀመሩ በማኅበረሰቡ ውስጥ መኖራቸው፣ የቲቢ በሽታ ቁጥጥርና ክትትል ላይ ትልቅ ተግዳሮት መደቀኑም ተጠቁMል፡፡

በአገሪቱ የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከ60 እስከ 70 በመቶ የበጀት ክፍተት መኖሩ ሌላኛውና ዋነኛው ችግር መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

የቲቢ ሕክምናና አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት በጦርነት መውደም፣  በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መፈናቀል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከተለያዩ አገሮች ተነስተው ወደ አገራቸው በሚመለሱበት ወቅት ለወራት በወደብ አካባቢ ታጭቀው መቆየት፣ የተመጣጠነ የምግብ እጥረትና የኮሮና ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ ለበሽታው መጨመር በምክንያትነት ቀርበዋል፡፡

በተለይ ደግሞ በከተሞች አካባቢ ያለው የቲቢ በሽታ ሥርጭት በጣም አስደንጋጭና ከአገሪቱ አማካይ ቁጥርም እጅግ የላቀ መሆኑ ተመልክ~ል፡፡

እንደ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረርና ሸገር ከተሞች የበሽታው ሥርጭት ከመቶ ሺሕ ሰዎች ከ208 እስከ 284 ድርሻ ይይዛሉ፡፡ ይህም በከተሞች አካባቢ ያለው ሥርጭት በሁለት እጥፍ መጨመሩን የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህም የብዙ ምክንያቶች ድምር ውጤት ነው፡፡ የኑሮ ውድነት፣ ድህነት፣ ፍልሰት፣ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት፣ የስኳር በሽታ፣ የአደንዛዥ ዕፅ መጠቀምና የቲቢ መመርመሪያ መሣሪያ  የአቅርቦት ውስንነት እንደ መንስዔ ከተጠቀሱት ውስጥ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት አደረግኳቸው ባላቸው ምልከታዎች የቲቢ በሽታ በከተሞች አካባቢ በእጅጉ መስፋፋቱን ያመለከተ ሲሆን፣ በሽታው በስፋት በተገኘባቸው ከተሞች ላይ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚተገበር ፕሮጀክት በ7.5 ሚሊዮን ዶላር መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

የሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነት ማነስና በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣው ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰት ለሥርጭቱ መባባስ ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን ለሪፖርተር የገለጹት፣ በድርጅቱ የተላላፊ በሽታዎች አማካሪ የሆኑት  የውልሰው ካሴ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

‹‹ብዙ ሰዎች ወደ ከተማ የሚያደርጉት ፍልሰት በሽታው እንዲስፋፋ ከማድረጉም ባሻገር በቂ የምርመራና የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኙ አንዱ ፈተና ነው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተጨናነቀ የኑሮ ሁኔታ መኖር በቂ ያልሆነ የጤና ተደራሽነት ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ ኅብረተሰቡን ያማከለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ አለመሠራት፣ አድልዎና መገለል መኖር  ዛሬም  ያልተቀረፉ ችግሮች መሆናቸውን የውልሰው (ዶ/ር) ያስረዳሉ፡፡

 ባለፉት አምስት ዓመታት በመንግሥትና በአጋር አካላት በተሰበሰበ መረጃ፣ በአዲስ አበባ በቲቢ የተያዙ ሰዎች በ25 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በድሬዳዋ 81 በመቶ፣ በሐረር 78 በመቶ እና በሸገር ከተማ 21 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በአራቱ ከተሞች ያለውን ችግር ለመፍታት ወደ ሥራ የገባው የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት የቀረፀውን የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ‹‹ሪች ኢትዮጵያ› የተባለው አገር በቀል ድርጅት እንዲሠራ ተሰጥቶታል፡፡ ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው ፕሮጀክቱ የቲቢ በሽታ ምርመራን ሕክምናና ልየታን በማሳደግ በተለያዩ ከተሞች ላይ ያለውን ሥርጭት ለመቀነስ ያለመ ነው፡፡

የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ባለፈው መጋቢት ‹‹የአገር በቀል ድርጅቶች ትስስር ፕሮጀክት አንድ›› አማካይነት በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላና በሶማሌ በአርሶና አርብቶ አደሮች አካባቢ ለሚተገበረው የቲቢ መከላከልና ሕክምና ፕሮጀክት የስድስት ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ ማስታወቁ መዘገባችን ይታወሳል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...