Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል ማስገንቢያ ከተዘጋጀው ኩፖን ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ...

ለወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል ማስገንቢያ ከተዘጋጀው ኩፖን ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ መጥፋቱ ተገለጸ

ቀን:

ለወሎ ተርሸሪ ኬር የሕክምናና የማስተማሪያ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ ለማዋል ወደ ተለያዩ ክልሎችና በውጭ አገሮች በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች በኩል ይሸጣል ተብሎ ተሠራጭቶ ከነበረው ኩፖን የብር መጠኑ 9,388,635.19 የሚያወጣው መጥፋቱ ተገለጸ፡፡

ለወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል ማስገንቢያ ከተዘጋጀው ኩፖን ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ መጥፋቱ ተገለጸ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ለገቢ ማሰባሰቢያ ከተዘጋጁ ኩፖኖች ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡት ጠፍተዋል

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2015 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲትና ክዋኔ ኦዲት ሪፖርቱን ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ለምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው፣ የፕሮጀክቱ የሥራ አመራር ቦርድ፣ በአገር ውስጥ ተሰብስቦ ባንክ ማስገባት የነበረበት 7,705,455 ብር ያልገባ፣ እንዲሁም ያልተመለሰ ቶምቦላ ብር 20,640.00 በውጭ አገሮች ለኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ተሠራጭቶ የጠፋ በሚል፣ በአጠቃላይ የ17,114,720.19 ብር የዕዳ ስረዛ መደረጉም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የሆስፒታሉ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የፕሮጀክቱ የሥራ አመራር ቦርድ ከወሎ  ዩኒቨርሲቲ ጋር ነሐሴ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ባደረጉት የፕሮጀክት ርክክብ ስምምነት መሠረት፣ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ የፕሮጀክቱ የሥራ አመራር ቦርድ ግዴታዎችና ኃላፊነቶች ውስጥ፣ ለፕሮጀክቱ ራሱን የቻለ አንድ ሕንፃ ለመገንባት የሚውል ሀብት በማፈላለግ በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ተንቀሳቅሶ የፋይናንስ፣ የግንባታ ቁሳቁሶች፣ የሕክምና መሣሪያዎችና ሌሎች ሀብቶችን በማሰባሰብና ከኅብረተሰቡ በተሰበሰበው ገንዘብ የአንድ ሕንፃ ግንባታ ወጪ ሙሉ በሙሉ ሸፍኖ በመሥራት ለዩኒቨርሲቲው እንደሚያስረክብ በግልጽ ቢቀመጥም፣ ኦዲቱ እስከተከናወነበት ቀን ድረስ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ (የፕሮጀክቱ የሥራ አመራር ቦርዱ) ምንም ዓይነት ሕንፃ መገንባት አለመቻሉም  ተገልጿል፡፡

ለወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል ማስገንቢያ ከተዘጋጀው ኩፖን ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ መጥፋቱ ተገለጸ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ለገቢ ማሰባሰቢያ ከተዘጋጁ ኩፖኖች ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡት ጠፍተዋል

የወሎ ተሪሸሪ ኬር ሕክምናና የማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ ከሕዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብና ቁሳቁስ ኦዲት በማስደረግ ሰነዶችን ጨምሮ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ እንዲያስረከብና የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ የሥራ ጊዜውን አጠናቆ እንዲዘጋ በግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ቢወሰንም፣ ኦዲቱ እስከተከናወነበት ቀን ድረስ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ በውሳኔው መሠረት የሥራ ጊዜውን አጠናቆ አለመዘጋቱ ታውቋል፡፡

የግንባታና የሕክምና ቁሳቁስ ወጪን ጨምሮ 5.5 ቢሊዮን ብር ያህል ይፈጃል የተባለው ወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት፣ ኅዳር 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ነበር፡፡

ከደሴ በስተሰሜን ሰባት ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ጢጣ በ470 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው የተጀመረው ወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል፣ አምስት ዕርከኖች (ሎቶች) ሲኖሩት፣ እስከ 2010 ዓ.ም. አጋማሽ ድረስ ሁሉም የሕንፃ ክፍሎች ወደ ግንባታ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡

የመሠረት ድንጋዩ ሲቀመጥ፣ የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኰንን፣ የወቅቱ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜና የፕሮጀክቱ የበላይ ጠባቂ ሼሕ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ ተገኝተው ነበር፡፡ በወቅቱም ግንባታው በ2012 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ ተነግሮ ነበር፡፡

ከዲዛይን ማሻሻል ጋር በተያያዘ ግንባታው የዘገየውና በግንቦት 2009 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረው ወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል፣ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ 700 ያህል ተኝተው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ በተመላላሽነት እንዲታከሙ እንደሚያስችል በወቅቱ ተነግሮ ነበር፡፡

ከ1,500 በላይ አዲስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በተወሰኑ የሕክምና መስኮች ከ200 በላይ ስፔሻላይዜሽንና ሰብ ስፔሻላይዜሽን ሐኪሞችን፣ ለሥራ ላይ ሙያተኞች አጫጭር ሥልጠና ይሰጣል ተብሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ለሆስፒታሉ ግንባታ ከቴሌቶንና ከቶምቦላ 60 ሚሊዮን ብር ያህል የተገኘ ሲሆን፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲም  በየዓመቱ በጀት በመጠየቅ የሚገነባው ነው፡፡ 

የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ኦዲት ዕቅድና ክንውን ሪፖርት የተጠናቀረው ከየካቲት 2015 ዓ.ም. እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ሲሆን፣ ሆስፒታሉ የተካተተውም በሕዝብ ጥያቄ መሠረት መሆኑ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...