Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹…እነኚህ ፈረንጆች እኮ የማይሠሩት ነገር የለም…››

ትኩስ ፅሁፎች

ቻርልስ ሚኬል እንደጻፈው ምኒልክ ከእስቴቬኒን ጋር ሲጫወቱ እስቲቬኒን የሲኒማን መኖር አጫወታቸው፡፡ ‹‹ሲኒማ ምንድነው እሱ?›› ብለው ጠየቁ፡፡ እሱም የሲኒማን ታሪክ ዘርዝሮ ካስረዳ በኋላ ለማስመጣት ፈልጎ ቄሶችን ፈርቶ መተውን ነገራቸው፡፡ ምኒልክ ‹‹ቄስ ይኑር አይኑር እሱን ተወውና ይሔን ነገር ለማየት ስለምፈልግ ቶሎ ብለህ አስመጣ›› ብለው አዘዙት፡፡ በ1889 ዓ.ም. ፕሮጀክተሩ ከነፊልሙ መጣ፡፡ ምኒልክም መኳንንቶቻቸውን ይዘው ሚያዝያ 1 ቀን ፊልሙን ለመመልከት ከእልፍኝ ተገኙ፡፡

ፊልሙ ሃይማኖት ነክ ሆኖ የሚያሳየው የክርስቶስን ታሪክ ነበር፡፡ ክርስቶስ በባሕር ላይ እየተራመደ በእግሩ ሲሔድ በታየበት ጊዜ መኳንንቱም ሁሉም ተነስተው እጅ ነሱ፡፡ ፊልሙ አልቆ ከራስ መኰንን ጋር በሚጫወቱበት ጊዜ ምኒልክ ‹‹…እነኚህ ፈረንጆች እኮ የማይሠሩት ነገር የለም፡፡ ሁሉንም ነገር ሲሠሩ የሰው ነፍስ ብቻ መሥራት አልቻሉም›› ብለው ተናገሩ፡፡

የመጀመርያው የሕዝብ ሲኒማ ቤት 1890 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡ ሲኒማ ቤቱን የከፈተው አንድ ከአልጄሪያ የመጣ ፈረንሳዊ ነው፡፡ ይህን በዘመኑ የማይታመን ምትሀት መሰል ነገር የሚያየው ሰው ሕዝብ የሲኒማ ቤቱን ‹‹ሰይጣን ቤት›› ብሎ ሰየመው፡፡ በተለይ ቀሳውስት ሕዝቡ ከሰይጣን ቤት እየሔደ ሰይጣን እንዳያይ እያሉ ስላወገዙ ሲኒማ ቤቱ ከሰረ፡፡ ባለቤቱም የሲኒማ ማሳያውን ዕቃ አዲስ አበባ ለነበረው የኢጣሊያ ሚኒስትር ለቺኮዲኮላ ሽጦ አገር ጥሎ ወጣ፡፡

– ጳውሎስ ኞኞ፣ ‹‹አጤ ምኒልክ›› (1984)

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች