Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢትዮጵያ ለ33ኛው ኦሊምፒያድ ሚኒማ ባላሟላችባቸው ርቀቶች ያልተሟጠጠ ዕድል እንዳላት ተገለጸ

ኢትዮጵያ ለ33ኛው ኦሊምፒያድ ሚኒማ ባላሟላችባቸው ርቀቶች ያልተሟጠጠ ዕድል እንዳላት ተገለጸ

ቀን:

አገሮች ዘር፣ ቀለምና ሃይማኖት ሳይከፋፍላቸው በአንድ የኦሊምፒክ መንደር ተሰባስበው በተለያዩ ስፖርታዊ ክንውኖች የሚገናኙበት ታላቅ ድግስ እንደሆነ የሚነገርለት የኦሊምፒክ ጨዋታ፣ ዘንድሮ ለ33ኛ ጊዜ በፈረንሣይ ፓሪስ ይካሄዳል፡፡ ከአንድ ወር ብዙም ያልዘለለ ጊዜ የቀረው ፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ እንደሚጀመርም ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ ለ33ኛው ኦሊምፒያድ ሚኒማ ባላሟላችባቸው ርቀቶች ያልተሟጠጠ ዕድል እንዳላት ተገለጸ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ከ20 ዓመት በታች የ10,000 ሜትር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበው
ቢንያም መሐሪ

በአትሌቲክሱ በተለይም በረዥም ርቀትና በማራቶን በጠንካራ አትሌቶች እንደምትወከል የምትጠበቀው ኢትዮጵያም፣ በወንዶች 800 ሜትር በስተቀር፣ በአብዛኛው ለፓሪስ ኦሊምፒክ ተሳታፊነት የሚያበቃትን ሚኒማ አሟልታ በዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡ ሰዓት (ሚኒማ) ባልተሟላባቸው ርቀቶች የመጨረሻው ቀነ ገደብ የሚያበቃው ሰኔ 23 ቀን በመሆኑ፣ በርቀቱ የሚጠበቁ አትሌቶች ለተሳትፎ የሚያበቃቸውን ሰዓት ለማሟላት ዕድሉን እንደሚጠቀሙበት ጭምር እየተነገረ ነው፡፡

የፓሪስ ኦሊምፒክ ዝግጅትን በጋራ እያከናወኑ የሚገኙት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለፈው ቅዳሜ ሰኔ 8 ቀን በስፔን ኔርሀ ከተማ በተደረገ የኦሊምፒክ መምረጫ ውድድር ላይ በ10,000 ሜትር ወንዶች 13 እና በሴቶች 14 አትሌቶችን አወዳድረው በሰዓታቸው ብቁ የሆኑትን አትሌቶች ይፋ አድርገዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሁለቱ ርቀቶች ለመወዳደር እንደ መሥፈርት ያስቀመጠው ሰዓት 27፡00፡00 ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በሁለቱም ርቀቶች በሁለቱም ፆታ መሥፈርቱን የሚያሟሉ በርካታ አትሌቶች አሏት፡፡ ይሁንና ብዙዎቹ አትሌቶቹ በሁለቱም ርቀቶች ማለትም በ5,000 እና በ10,000 ሜትር በፓሪስ ኦሊምፒክ መሳተፍ የሚያስችል ሰዓት ስላላቸው፣ የኦሊምፒክ መምረጫ ውድድር ማዘጋጀት አስፈልጓል ተብሏል፡፡

በዚሁ መሠረት ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው የኦሊምፒክ መምረጫ ውድድር ላይ ከተሳተፉት አትሌቶች መካከል፣ በወንዶች ዮሚፍ ቀጄልቻ 26፡31፡01 አንደኛ፣ በሪሁ አረጋዊ 26፡31፡13 ሁለተኛና ሰሎሞን ባረጋ የቶኪዮ ኦሊምፒክ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ፣ በቀጥታ ተሳታፊ ቢሆንም በዕለቱ በተደረገው ውድድር ግን ርቀቱን 26፡34፡43 ሦስተኛ በመሆን ማጠናቀቁ ይታወቃል፡፡

በዕለቱ በተደረገው የመምረጫ ውድድር ላይ ዕድሜው ከ20 ዓመት በታች ሆኖ የተወዳደረው ቢንያም መሐሪ፣ ርቀቱን 26፡37፡65 በማጠናቀቅ በዕድሜው ያስመዘገበው ሰዓት የዓለም ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡

በባለሙያዎች አስተያየት፣ ቢንያም መሐሪ በርቀቱ ቀነኒሳ በቀለን እንደሚያስታውሳቸው በመግለጽ ከወዲሁ አድናቆታቸውን እየለገሱት ይገኛል፡፡ አትሌቱ በሁለቱም ርቀቶች ማለትም 10,000 እና 5,000 ሜትር ለፓሪስ ኦሊምፒክ ስለመመረጡ ጭምር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በመካከለኛ ርቀት በፓሪስ ኦሊምፒክ የሚያሳትፉትን ሰዓት 3፡33፡50፣ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው የኦሊምፒክ መምረጫ ውድድር እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ ሚኒማውን የሚያሟሉ አትሌቶች ሳታሳውቅ መቆየቷ የሚታወቅ ነው፡፡

ይሁንና በውድድሩ ከተሳተፉት 10 አትሌቶች መካከል አብዲሳ ፈይሳ 3፡32፡37 በማጠናቀቅ፣ እንዲሁም እሱን ተከትሎ ሳሙኤል ተፈራ 3፡32፡81 ተከታትለው በመግባት መሥፈርቱን በማሟላት ሁለቱ አትሌቶች በርቀቱ ወደ ፓሪስ እንደሚያቀኑ አረጋግጠዋል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሦስተኛውንና ተጠባባቂውን አትሌት ለመምረጥ ቀነ ገደቡ እስከሚያቃበት ድረስ ተጨማሪ የሰዓት ማሟያ ውድድሮችን ማመቻቸት እንደሚጠበቅበት እየተነገረ ይገኛል፡፡

ሌላው ሚኒማ ያልተሟላበት ርቀት 800 ሜትር ነው፡፡ በርቀቱ የተቀመጠለት መሥፈርት 1፡33፡70 ሲሆን፣ በውድድሩ በአጠቃላይ አምስት አትሌቶች ቢሳተፉም፣ ሁሉም ማሟላት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

በመምረጫ ውድድሩ የተሳተፉት አትሌቶች ያስመዘገቡት ጄኔራል ብርሃኑ 1፡45፡45፣ ኤፍሬም መኮንን 1፡46፡10፣ መርሲሞይ ካሳሁን 1፡46፡22፣ ዮሐንስ ተፈራ 1፡47፡00 እና ሚሊዮን በቀለ 1፡51፡67 በመሆኑ ለፓሪስ ኦሊምፒክ እንደማያበቃቸው ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቴክኒክና ሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ቢልልኝ መቆያ አስተያየት መሠረት፣ በ800 ሜትር የሚኒማ ማሟያ ውድድሮችን ማግኘት ስለሚቻል፣ ዓለም አቀፉ ተቋም ያስቀመጠው የመጨረሻ ቀነ ገደብ እስኪጠናቀቅ ድረስ ጥረት ይደረጋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...