Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዝንቅሀረር ከግራዞኒ መንደር ምን ትማራለች?

ሀረር ከግራዞኒ መንደር ምን ትማራለች?

ቀን:

ኮሎዲ በምትባለው መንደር ውስጥ የሚገኘው ቪላ ጋርዞኒ በሉካ ግዛት (ቱስካኒ፣ ጣሊያን) ድንበር ላይ ቀጥ ብሎ ወደተራራ በሚወጣ ዳገት ላይ በ1652 ወይም ከዚያ ትንሽ ቀደም ብሎ የተመሠረተ መንደር ነው። መስራቾቹም የጋርዞኒ ቤተሰቦች ሲሆኑ በውስጡ አንድ ትልቅና ውብ ቤተ መንግሥት አለ። ወደ ጋርዞኒ ለመውጣት የሚቻለው በእግር ነው። ቀደም ባሉት ጊዜያት አቀማመጡ ከጠላት ለመከላከል ይረዳ ነበር። በዳገታማ ስፍራ ላይ የተመሠረተው ጋርዞኒ ከሥሩ ካለችው ከኮሎዲ መንደር ጋር የተያያዘ ነው። ኮሎዲ ደግሞ አፍንጮ (Pinocchio) የተፈጠረባት ናት። በጣሊያንኛ Il Parco di Pinocchio a Collodi, ትርጉሙም በአፍንጮ ስም የተመሠረተ የመዝናኛ ስፍራ ነው። “የአፍንጮ የትውልድ ስፍራ” እየተባለም ይጠራል።

ሀረር ከግራዞኒ መንደር ምን ትማራለች? | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ይህን ያህል ለመንደርደሪያ የሚያህል ሐሳብ ከሰጠሁ በኋላ ለማውሳት የምፈልገው ሀረር ከዚች መንደር ምን ትማራለች?” የሚለውን ነው። እንደሚታወቀው ሀረርም ኮረብታ ላይ የተመሠረተች ከመሆኗም በላይ ጥንታዊ ናት። እንደጋራዞኒ አንዱ ቤት ከሌላው ቤት ጋር ተቆላልፈው የተሠሩባት ናት። ቤቶቹንና አጥሮቹን ካላፈራረሱ በስተቀር የውኃና ፍሳሽ መዘርጋት በጣም አስቸጋሪ ነው። ይህ ደግሞ ጥንታዊ መልኩን ስለሚቀይረው የማይታሰብ ነው። እርግጥ ነው፣ አንዳንድ ሰዎች “ሀረር እየፈረሰች የተሠራች ስለሆነች ለምን አጥሮችና መንገዶች ፈርሰው በዘመናዊ መልክ ለምን አይሠራም?” ብለው አስተያዬታቸውን ይሰጣሉ። ይህ አስተያዬት ጥንታዊነቷን ስለሚያሳጣት አግባብ አይደለም።

- Advertisement -

ማድረግ የሚቻለው የከተማዋን ጥንታዊ ሳይጎዱ በጥንቃቄ የውኃና ፍሳሽ ማውረጃ መሥራት። በሥዕሉ ላይ በስሱም እንደምንመለከተው በግንብ አጥሩ ላይ የፍሳሽ መውረጃ ውስጥ ለውስጥ ገብቷል። ፕላስቲኩ የሚታየው ተመሳስሎ እስኪለሰን ነው። ወለሉ ላይም የውኃ መስመር ተዘርግቷል። ሁለቱም የተዘረጉት ጥንታዊ መልኩን ሳያጠፉ ነው።

ሀረር እንዲህ ያለውን ብዙ ወጭ የሚያስወጣ ተግባር ለማከናወን ባያስችላት የቢፒሲ ወፍራም ቱቦ በመዘርጋት የውኃና የፍሳሽ መውረጃ ችግርን ለመቅረፍ የምትችል ይመስለኛል።

  • ተሾመ ብርሃኑ ከማል
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...