Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበአዲስ አበባ የሚታየውን የአየር ብክለት መቆጣጠር ካልተቻለ ከ 2,000 በላይ ሰዎች...

በአዲስ አበባ የሚታየውን የአየር ብክለት መቆጣጠር ካልተቻለ ከ 2,000 በላይ ሰዎች እንደሚሞቱ ተገለጸ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን የአየር ብክለት መቆጣጠርና መከላከል ካልተቻለ፣ በ2017 ዓ.ም. እስከ 2,700 ሰዎች እንደሚሞቱ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በባለሥልጣኑ ጥናት መሠረት እስከ 2025 ዓ.ም. ድረስ ምንም ዓይነት የመከላከል ሥራ ካልተሠራ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር 6,000 እንደሚደርስ፣ ዓርብ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባለሥልጣኑ የተሽከርካሪ ብክለት ቁጥጥር አፈጻጸም መመርያን ይፋ ሲያደርግ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአየር ንብረትና የአማራጭ ኢነርጂ ዳይሬክተር አቶ ሰይድ አብደላ እንደገለጹት፣ ‹‹ለከተማዋ የአየር ብክለት በከፍተኛ ደረጃ መጨመር እንደ ዋነኛ ምክንያት የተቀመጠው ከተሽከርካሪዎች የሚወጣ በካይ ጭስ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ በሰዎች ጤናና በአገር ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

በከተማው እየጨመረ ለመጣው የአየር ብክለት መነሻ ምክንያት የተሽከርካሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመርና ከተሽከርካሪዎች መካከል አብዛኞቹ ያረጁ መሆናቸው ነው ተብሏል፡፡ ያረጁ ተሽከርካሪዎች ሞተራቸው ነዳጅን በአግባቡ የማያቃጥል በመሆኑ፣ የካርቦን ልቀት በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ለአየር ሙቀት መጨመር ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ለከተማዋ የአየር ብክለት ተሽከርካሪዎች 28 በመቶ፣ ባዮማስ ነዳጅ 18.3 በመቶና የአፈር አቧራ 17.4 በመቶ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸው፣ ‹‹ይህንንም ለመከላከል የተሽከርካሪ በካይ ጋዝ የቁጥጥርና ክትትል መመርያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፤›› ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ በበኩላቸው፣ ከተሽከርካሪዎች የሚወጣው በካይ ጋዝ በከተማዋና በነዋሪው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ በጥናት ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

‹‹በኢትዮጵያ ከሚገኙ ተሽከርካሪዎች 60 በመቶ ያህሉ በአዲስ አከባ ከተማ ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ተሽከርካሪዎች በእርጅና፣ በብልሽት፣ በመንገድ መጣበብና በሌሎችም ምክንያቶች ከፍተኛ በካይ ጭሶችን በማውጣት በሰዎች ጤና ላይ የመተንፈሻ አካላት ችግር፣ ሳንባ ካንሰር፣ አስም፣ የልብ ሕመምና ሞትን በማስከተል ላይ ናቸው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

በእንስሳትና በዕፅዋት ደኅንነት፣ በውኃ አካላትና የከተማን ዕይታ በማወክ ጉዳቶችን እያስከተሉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

አቶ ዲዳ በከተማዋ የጤና፣ የማኅበራዊና የኢኮኖሚ ችግር እያስከተለ ያለውን የአካባቢ ብክለት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለተሽከርካሪዎች የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ደረጃ (ስታንዳርድ) የአፈጻጸም መመርያ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

መመርያው ከተሽከርካሪዎች የሚወጣውን የጭስ ብክለት ልቀት መጠን በመቀነስ፣ የሕዝብ ጤንነት ማስጠበቅና የአየር ብክለትን መከላከልና መቀነስ ያስችላል ብለዋል፡፡

በከተማም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ የንፁህ ቴክኖሎጂዎችንና ነዳጅ መጠቀምን የሚያበረታታ፣ ለአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው የበለጠ ነዳጅ ቆጣቢና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን እንዲያመርቱ መመርያው የሚያበረታታ መሆኑንም አቶ ዲዳ አክለው ተናግረዋል፡፡  

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እ.ኤ.አ. በ2019 ከአየር ክብለት ጋር በተያያዘ 1,600 ሰዎች መሞታቸውን፣ ከብክለቱ ጋር ተያይዞ ከተፈጠረ ሕመምና ሞት 78 ሚሊዮን ዶላር ጉዳት መድረሱን የዓለም ባንክን ጥናት ጠቅሶ ባለሥልጣኑ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...