Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለሠራተኞቹ አበድሮት የተገኘው 8.9 ሚሊዮን ብር እንዲጣራ ፓርላማ አሳሰበ

የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለሠራተኞቹ አበድሮት የተገኘው 8.9 ሚሊዮን ብር እንዲጣራ ፓርላማ አሳሰበ

ቀን:

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሥር የሚተዳደረው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ ለ94 ሠራተኞች ከ8.9 ሚሊዮን ብር በላይ ማበደሩ በኦዲት በመገኘቱ፣ ስለብድሩ ትክክለኛነትና ተከፋይ ስለመሆኑም ተጣርቶ እንዲቀርብ ፓርላማ አሳሰበ፡፡

ይህ የተገለጸው ኮርፖሬሽኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የ2015 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲት ግኝት ማስተካከያ መርሐ ግብር አፈጻጸም አስመልክቶ በቀረበው የጽሑፍ ማብራሪያ ላይ ነው።

በዚህ የሪፖርቱ ክፍል ስምንት የኦዲት ግኝቶች፣ የኦዲት አስተያየቶች፣ የአስተዳደር ውሳኔዎችና እስከ መጋቢት ወር 2016 ዓ.ም. ድረስ የተፈጸሙ ክንውኖች ተጠቅሰዋል።

- Advertisement -

ከግኝቶቹ መካከል አንዱ የሆነው የሠራተኞች የብድር ሒሳብ በአጠቃላይ 8,921,736 ብር ያልተለመደ (Abnormal balance) ቀሪ ሒሳብ ያሳየ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከ94 ሠራተኞች ጋር የተያዘው ገንዘብ ከ15,001 ብር እስከ 811,991 ብር የሚደርስ ባላንስ ያላቸው በአጠቃላይ 6,106,563 ብር፣ ሲሆን ሁለት ሠራተኞች ደግሞ ከ500,000 ብር በላይ መበደራቸው በኦዲት ተረጋግጧል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በስም ተለይተው የተጠቀሱት ሁለት ሠራተኞች ያለባቸው ብድር አንደኛው 811,991 ብር፣ ሌላኛው ደግሞ 570,735 ብር በድምሩ 1,382,729 ብር እንደሆነ ተጠቅሷል።

በሪፖርቱ ላይ የተጠቀሰው ግኝት እንደሚያብራራው፣ እነዚህ አኃዞች በቅጥር መቋረጥ ወይም በሌሎች ጉዳዮች ሊከፈሉ ይሚሉ ቢሆንም የመጠኑ ትክክለኛነት ሊጣራና ሊረጋገጥ ይገባል ተብሏል።

ስለኦዲቱ በተሰጠው አስተያየት፣ ‹‹አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ የዕርምት ዕርምጃ በጊዜው እንዲወሰድ›› የሚል ሲሆን፣ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተፈጻሚ እንዲሆን ትዕዛዝ የተሰጠበት አስተዳደራዊ ውሳኔም የዘርፉ አጠቃላይ የሠራተኞች ተሰብሳቢና ተከፋይ ሒሳቦች ሌጀሮች ተጣርተው እንዲቀርቡ አዟል።

የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ ይህን የኦዲት ግኝት በተመለከተ እስከ መጋቢት ወር 2016 ዓ.ም. ድረስ ተፈጽሟል ተብሎ የቀረበው ክንውን እንደሚያብራራው፣ ሰነዶች እስከ 2003 ዓ.ም. የሚፈለጉ በመሆናቸውና ኮርፖሬሽኑም ሰነዶችን በመፈለግ ላይ መሆኑን በመጥቀስ፣ በአጠቃላይ ከ8,921,736 ብር ያልተለመደ (Abnormal balance) ውስጥ ለ3,797,536.10 ብር ማስተካከያ እንደተሠራለት ተጠቅሷል።

በተያያዘም ካለው ሒሳብ (Normal Balance) ለ515,477.40 ብር ማስተካከያ እንደተሠራ በግኝቱ ተመላክቷል።

በኦዲት ግኝቱ ከ94 ሚሊዮን ብር ሒሳብ ከተገኘባቸው ሠራተኞች የ29 ሠራተኞች አካውንት ተጣርቶ ክሊራንስ እንዲያገኙ መደረጉ የተገለጸ ሲሆን፣ ቀሪው በሠራተኞች አካውንት ተመዝግቦ የሚገኝ የገንዘብ መጠን (Balance) በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የኦዲት ግኝቱ የጽሑፍ ማብራሪያ ከመጋዘን የሚወጣ ንብረት (Store Delivery) በቃል የሚታዘዝ መሆኑንና ከግምጃ ቤት ከወጣ በኋላ የማጓጓዣ ማዘዣ የሚዘጋጀውና የሚፈርመው በአንድ ሰው መሆኑንና ይህም ሳይፀድቅ የተጠቀሰ ሲሆን፣ የውስጥ ቁጥጥር መኖሩ የሚያጠራጥርና በሒደቱ ውስጥ የተሳተፉ ሠራተኞች መመርያውን በደንብ ያልተረዱ ወይም ለቦታው ብቃት የሌላቸው መሆኑን ያስረዳል።

ለዚህ ግኝት የተሰጠው አስተያየት የኮርፖሬሽኑ አስተዳደር ለችግሩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት አስፈላጊ የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲወሰድ ነው፡፡ የኮርፖሬሽኑ አስተዳደር ማሳለፍ ያለበት ውሳኔ ነው በሚል ደግሞ ‹‹ለሚመለከታቸው ለሁሉም ሠራተኞች ተገቢው ሥልጠና እንዲሰጥ፣ በተጨማሪም የሚገለገሉበት አሠራር አውቶሜሽን እንዲዘጋጅለት›› የሚል መመርያ በተመሳሳይ እስከ መጋቢት 2016 ዓ.ም. ድረስ እንዲያስፈጽም አቅጣጫ ተሰጥቶት እንደነበር ሪፖርቱ ያትታል።

ኮርፖሬሽኑም በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ የሽያጭ ማዘዣ (Delivery note) በቃል ትዕዛዝ መሥራት ለፎርጅድ ያጋለጠ በመሆኑና ይህ ማዘዣ በአንድ ሰው (ኃላፊ) ብቻ የሚፈረመው ስህተት መሆኑን በማመን እንዲስተካከል፣ የደረሰኙን ግልባጭ (copy) በማያያዝ ተልኮ ሥልጠና እንዲሰጥ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥራ አመራር ጥያቄ ማቅረቡን ገልጿል። በሥራ አመራር በኩልም ቁሳቁስ ማሟላትና ሥልጠና መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...