Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየአፋርኛ የፊደል ገበታ 50ኛ ዓመትና የአፍ መፍቻ ቀን

የአፋርኛ የፊደል ገበታ 50ኛ ዓመትና የአፍ መፍቻ ቀን

ቀን:

ዓለም አቀፉ የባህል ተቋም ዩኔስኮ በድረ ገጹ እንደሚገልጸው፣ ለማኅበረሰቦች ዘላቂያዊ ግንኙነት የባህልና የቋንቋ ብዝኃነት አስፈላጊነት አለው።  መቻቻልና መከባበርን የሚያጎለብቱ የባህልና የቋንቋ ብዝኃነትን ለመጠበቅ የሚሠራው ለሰላም በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት ነው። 

የመድበለ ቋንቋና የመድበለ ባህል ማኅበረሰቦች በቋንቋዎቻቸው ባህላዊ ዕውቀቶችንና ባህሎችን በዘላቂነት የሚያስተላልፉና የሚጠብቁ ናቸው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ 40 በመቶው ሕዝብ በሚናገሩትና በሚረዱት ቋንቋ የትምህርት ዕድል ባይኖራቸውም የመድበለ ቋንቋ ትምህርት ጠቃሚነቱ በተለይም በቅድመ ትምህርት ቤትና በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚታይ ነው።

የአፋርኛ የፊደል ገበታ 50ኛ ዓመትና የአፍ መፍቻ ቀን | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
በክብረ በዓሉ ከቀረቡት ትርዒቶች አንዱ

አንድ ሰው በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማሩ በትምህርት ቤት ውስጥ ስኬታማ ለመሆን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ለራስ ያለን ግምት ከፍ እንደሚያደርገው፣ ከልጅነት ጀምሮ የማወቅ ጉጉትን እንደሚያነቃቃና የዕውቀት ዕድገትን እንደሚያመቻች በዩኔስኮ ጥናት ተመልክቷል፡፡  

በአሁኑ ጊዜ 250 ሚሊዮን ሕፃናትና ወጣቶች አሁንም ትምህርት እንደማይከታተሉ፣ 763 ሚሊዮን ጎልማሶች መሠረታዊ የማንበብ ክህሎትን እንዳልተማሩ ተጠቁሟል። 

ከሰባት አሠርታት በፊት በባንግላዴሽ የተጀመረው በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመጠቀምና በውስጡም ባህሎችን ጠብቆ የማቆየት ንቅናቄ ከሰመረ በኋላ፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመጠቀም መብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመንግሥታቱ ድርጅት፣ በ1991 ዓ.ም. ባቀረበችው ምክረ ሐሳብ መሠረት፣ ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ ‹ፌብሩዋሪ 21› የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን ሆኖ እንዲከበር ተወስኗል፡፡

የዘንድሮው መሪ ቃል ‹‹በብዝኃ ቋንቋ መማር ትምህርትን ከትውልድ ትውልድ ለማሸጋገር ምሰሶ ነው›› (Multilingual Education is a Pillar of Intergenerational Learning) በየአገሮቹ የታሰበ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም በባንግላዴሽ ኤምባሲ አስተባባሪነት፣ በዩኔስኮና በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ትብብር በአፍሪካ አዳራሽ መታሰቡ ይታወሳል፡፡ 

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ ቀኑን ያሰበችው ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሲሆን፣ የአፍ መፍቻ ክብረ ቀኑንም ያያያዘችው ከአፍ መፍቻ ቋንቋነት ባለፈ የፌዴራል ቋንቋ የሆነው አፋርኛ የፊደል ገበታ የተቀረፀለት 50ኛ ዓመት ጋር ነው፡፡

‹‹የአገሪቱን ቋንቋዎችና ሥርዓተ ጽሕፈቶች እንደ ብሔራዊ ሀብትና ቅርስ መቀበል የቋንቋ ፖሊሲ አንዱ መርሕ ነው፤›› የሚለው የተጠቀሰበት መድረክን፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከአፋር ቋንቋ ባህልና ታሪክ አካዴሚ፣ ከሰመራ ዩኒቨርሲቲና ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል፡፡

‹‹የራስን ቋንቋ እንደ ሕዝብ ጠብቆ ማቆየት ለትውልድ ማስተላለፍ ቀላል ነገር አይደለም፤›› ያሉት በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣ ምክንያቱንም በቋንቋ ውስጥ ታሪክን፣ ባህልን፣ ቅርስን ለትውልድ የምናስተላልፍበት ትልቁና ብቸኛው መሣሪያ ነው በማለት ገልጸውታል፡፡

‹‹በትምህርት ሥርዓት ውስጥ በራስ ቋንቋ መማር፣ መጻፍ፣ ፊደል መቅረፅና መመራመር ያለው ፋይዳ ትልቅ በመሆኑ፣ ይህንን ቋንቋ ጠብቀው ያቆዩትን የአፋር አባቶች አመሰግናለሁ፤›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የቋንቋ ፖሊሲ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር መብት የሰጠ ቢሆንም፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋ መናገር ተፈጥሮ የለገሰችው መብት ጭምር እንደሆነ ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ አያይዘውም የአፋርኛ ቋንቋ ፊደል የተቀረፀበት 50ኛ ዓመት ስታከብሩ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን ጋር አያይዛችሁ መሆኑ የተለየ ትርጉም ያሰጠዋል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

መንግሥት ከአማርኛ በተጨማሪ አፋርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛና ትግርኛ የፌዴራል ቋንቋ እንዲሆኑ የወሰነ መሆኑንም ተከትሎ ለአተገባበሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ የአፋርን ባህልና የአኗኗር ዘይቤ የሚያስቃኙ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤት አሠራር እንዲሁም በአፋርኛ የተጻፉ መጻሕፍት ለዕይታ የቀረቡበት የባህል ዓውደ ርዕይ ተከፍቷል፡፡

በመድረኩ ከፌደራልና ከክልል የመጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በአፋር የባህል ውዝዋዜ፣ የባህል አልባሳትና ሙዚቃዎች ደምቆ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...