Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማትና የመሠረቱት መማክርት

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማትና የመሠረቱት መማክርት

ቀን:

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና (ቲቪኢቲ) ግለሰቦችን የሰው ኃይል ፍላጎት በዘመነ መልኩ ለማዘጋጀት፣ በተመረጡት የሥራ መስክ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ ተግባራዊ ክህሎቶችን፣ ዕውቀትንና ዕድሎችን ለማቅረብ አስፈላጊ ነው።

ቲቪኢቲ በትምህርትና በሥራ መካከል ያለውን ልዩነት ለማደላደል፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለመምራት፣ ማኅበራዊ እንቅስቃሴን በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪዎችንና የኅብረተሰቡን ፍላጎት በማሟላት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይታሰባል።

በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ በዝቅተኛና በመካከለኛ ደረጃ የሠለጠነ የሰው ኃይል ለማቅረብ ከሁለት ሺሕ በላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በሥራ ላይ እንደሚገኙ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋም መረጃ ያሳያል፡፡

- Advertisement -

እነዚህ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ያሉባቸውን ችግሮች በጋራ ለመፍታት እንዲሁም በሚወጡ ፖሊሲዎችና መመርያዎች ላይ ለመምከር ያስችላል የተባለ የአመራሮች ምክር ቤት ሰሞኑን መሥርተዋል፡፡

ከአንድ ክልል በላይ ተደራሽነት ያላቸው በፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ደረጃ ያሉ ተቋማትና በግል ዘርፉ ደግሞ የምሥረታ ጊዜያቸው ቆየት ያሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አመራሮች በምሥረታው መካተታቸውን የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋም ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በመንግሥትና በግል ባለቤትነት በሥራ ላይ ከሚገኙት መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች መሆናቸውን፣ የበርካታ ወጣቶችን ክህሎት በማሳደግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ሥራ እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የምክር ቤቱ መቋቋም የመንግሥትና የግል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የጋራ ችግራቸውን በጋራ እንዲፈቱና የየግል ልምዳቸውን እንዲጋሩ የሚያግዝ እንደሚሆን ብሩክ (ዶ/ር) አክለዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ በአገር ደረጃ በሚወጡ ፖሊሲዎችና መመርያዎች ላይ ለመወያየትና ለመገምገም የሚችሉበትን መድረክ የሚፈጥር ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ድጋፍና ክትትል በማድረግ ያለውን ሚና እንዲወጣ  ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምክር ቤቱ ከተመሠረተ በኋላ ውጤታማና ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ከተፈለገ  ባለድርሻ አካላት መሳተፍ ይገባቸዋል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ቀደም ሲል በዘርፉ አመራሮች መካከል ይካሄዱ የነበሩ ውይይቶችና ትብብሮች  መደበኛ ባልሆነ መንገድ ነበር ያሉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ናቸው፡፡

 የምክር ቤቱ መመሥረት ቀደም ሲል የነበሩ ግንኙነቶችን በመደበኛ ሁኔታ ማስቀጠልና ትብብሩን ውጤታማ ለማድረግን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም  ገልጸዋል።

‹‹በምናውቀው መንገድና በለመድነው ፍጥነት ብቻ የምንፈልገውን ውጤት ማስመዝገብ አንችልም፤›› ያሉት ሚኒስትሯ፣ የራሳችንን ፈጠራ እያከልን በትብብር መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት አመራሮች ምክር ቤትን እንዲመሩ በፕሬዚዳንትነት ከጄነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አቶ መለሰ ይግዛውን፣ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ከአዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አቶ ዳሌ_ጀንቦን፣ በጸሐፊነት ከሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አቶ መልካሙ_ባራሳ ተመርጠዋል።

የቴክኒክና ሙያ አመራሮች መማክርቱ የተመሠረተው ‹‹ብቁ መሪነት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት›› የሚል መሪ ቃልን ተንተርሶ መሆኑ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...