Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየኩዌትና የኢትዮጵያ ኤጀንሲዎች የደረሱት ስምምነት

የኩዌትና የኢትዮጵያ ኤጀንሲዎች የደረሱት ስምምነት

ቀን:

ወጣቶች በአገራቸው ሠርተው በሚፈልጉት ደረጃ ለውጥ ሳያመጡ ሲቀሩ አልያም የተሻለ ገቢን ለማግኘት ወደ ተለያዩ የዓረብ አገሮች ያማትራሉ፡፡ በዚህም በየዓመቱ በርካታ ወጣቶች በሕገወጥ ደላላም ሆነ በሕጋዊ መንገድ ከአገራቸው ወጥተው በተለያዩ የዓረብ አገሮች ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በሕገወጥ መንገድ በተለያዩ ደላሎች ተታለው ከአገር የሚወጡ ወጣቶች ተቆጥሮ የማያልቅ ግፍና በደል ሲደርስባቸው ማየት የተለመደ ነው፡፡

መንግሥት ከጥቂት ዓመታት በፊት ጀምሮ ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ ነው፡፡ ሆኖም ዛሬም ችግሮች አሉ፡፡

እነዚህንና መሰል ችግሮችን ለመፍታት ኢትዮጵያና ኩዌት በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት በጋራ ለመሥራት ከአንድ ዓመት በላይ ድርድር ሲያካሂዱ ቆይተው፣ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

የዜጎችን መብትና ክብር ለማስጠበቅ፣ የሚሰማሩበት የሥራ መስክ ለደኅንነታቸውና ለጤናቸው ሥጋት የማያስከትል እንዲሁም መድን፣ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማስጠበቅ የሚሉት የስምምነቱ አካል ናቸው፡፡

አንዳንድ ኤጀንሲዎች ሕግና መመርያውን ተከትለውና ለዜጎቻቸው አስበው በሕጋዊ መንገድ የበኩላቸውን ሲወጡ፣ በተቃራኒው ለዜጎች ሞትና መንገላታት ምክንያት የሚሆኑም አሉ፡፡

በሕገወጥ መንገድ ከአገር የሚወጡ ዜጎችን ለማስቀረትና ወደ ሕጋዊ ለማምጣት ሕገወጥ ደላላዎችን በመከላከል የዜጎችን ክብርና ደኅንነት ለማስጠበቅ የኢትዮጵያ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት አገናኝ ኤጀንሲ አሠሪዎች ፌዴሬሽን ከኩዌት ኤጀንሲዎች ማኅበር ጋር በጋራ ለመሥራት ስምምነት ማድረጉን ፌዴሬሽኑ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡

ስምምነቱ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመቀጠል ወደ ተለያዩ ዓረብ አገሮች የሚሄዱ ዜጎችን ጥቅምና ክብር ለማስጠበቅ እንዲሁም በሕገወጥ መንገድ ከአገር የሚወጡ ወጣቶችን ለማዳን የሚያስችል መሆኑንም ፌዴሬሽኑ  አስታውቋል፡፡

ሠራተኞች ከአሠሪዎቻቸው ጋር ያለመግባባት ችግሮች ሲያጋጥማቸው፣ ከአሠሪዎቻቸው ጠፍተው ወይም ተጣልተው ከቤት ሲወጡ ለጎዳና እንዳይጋለጡ፣ ደመወዝ በወቅቱ እንዲከፈላቸው በአጠቃላይም ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሔ ከማመቻቸት ጀምሮ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ  የኩዌት ኤጀንሲዎች ማኅበር የሚያከናውናቸው ተግባራት መሆናቸው በስምምነቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡

ስምምነቱ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጫና በቅርበት ተከታትሎ ከማስቀረት ባሻገር በርካሽ ጉልበት በማቅረብ በአሠሪዎቻቸው ዘንድ እንደ ርካሽ ዕቃ እንዲቆጠሩ ሲያደርጋቸው የነበረውን ችግር ለመፍታት እንደሚያስችል የፌዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት አቶ ሰኢድ አህመድ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል ሕገወጥ የሥራ ሥምሪት አሠራርን ለመከላከል ውጤታማ ዕርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው ያሉት አቶ ሰኢድ፣ በሳዑዲ ዓረቢያ፣ ዮርዳኖስና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ባሉ አገሮች ለሥራ በሕጋዊ መንገድ የሚሰማሩ ዜጎችን  ደኅንነት ለማስጠበቅ በሁለቱም አካላት የተደረገው ስምምነት በዋናነት ሰባት ዋና ዋና ነጥቦች መያዙን ተናግረዋል፡፡

ማኅበሩ በኩዌት ተቀጥረው የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መብታቸው እንዲጠበቅ የተቻለውን ሁሉ ማድረግ፣ ሁለቱም ወገኖች የተፈቀደላቸውና ፈቃድ ላላቸው መሥሪያ ቤቶች፣ ኤጀንሲዎችና ድርጅቶች ስምና አድራሻ ለሌላኛው ወገን ማቅረብ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተመዘገቡና ሙሉ ፈቃድ ያላቸው የግል ቅጥር ኤጀንሲዎች በተለይም ስማቸውና አድራሻቸው የተገለጸላቸው በሙሉ በኩዌት ውስጥ በነፃነት የሥራ ሥምሪት አገልግሎት የመሰማራት መብት እንዲኖራቸው ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ ከአሠሪዎቻቸው ጋር አለመግባባት የፈጠሩ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን መርዳትና መደገፍ፣ መጠለያና የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ ማድረግ የሚሉትና ሌሎችም በስምምነቱ የተጠቀሱ ነጥቦች ናቸው፡፡

በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ኤጀንሲዎች ግዴታቸውን ለመወጣት በስምምነት ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...