Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ሀብት ስኬት ፍቅር››

ትኩስ ፅሁፎች

‹‹በአንድ መንደር ውስጥ አንዲት ሴት ከቤቷ ውጭ ሦስት አዛውንቶችን ተቀምጠው አየች። ከዚያም አዝናላቸው ወደ ውጭ ወጥታ እዚህ ለረዥም ጊዜ እንደ ተቀመጣችሁ አይቻለሁ፣ ርቦአችሁ ይሆናልና እባካችሁ ወደ ቤት ግቡና የሚበላ ነገር ቅመሱ አለቻቸው። ከመካከላቸው አንዱ ሽማግሌ እንዲህ ሲል ጠየቃት። ‹ባለቤትሽ እቤት ውስጥ አለ?› አላት። እሷም ‹የለም ሥራ ነው› ብላ መለሰችላቸው። ሽማግሌዎቹም ‹እኛ ባለቤትሽ ሳይኖር ወደ ቤት ውስጥ መግባት አንችልም› አሏት። ሴትየዋም እሺ ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች። በመሸ ጊዜ ባሏ ከሥራው ሲመጣ፣ ውጭ ስለተቀመጡት ሰዎችና የሆነውን ሁሉ ነገረችው። እሱም ሄዳ ሽማግሌዎቹ ገብተው ምግብ እንዲበሉ ንገሪያቸው አላት። እሷም ‹ባለቤቴ ስለመጣ ምግብ ትበሉ ዘንድ እየጋበዛችሁ ነው። እባካችሁ ወደ ውስጥ ግቡና ከእኛ ጋር ምግብ እንብላ አለቻቸው። 

እነሱም ሦስታችንም አብረን ወደ ቤታችሁ አንገባም ነገር ግን ከሦስታችን አንዳችንን መርጠሽ ወደ ቤት ገብተን ምግብ እንቀምሳለን በማለት ከሽማግሌዎቹ አንዱ ተናገረ። ወደ አንዱ ጓደኛውም እየጠቆመ ስሙ ‹‹ሀብት›› ይባላል። ከእናንተ ጋር የሚመገብ ከሆነ ቤታችሁ ሁል ጊዜ በሀብት ይሞላል። ወደ ሌላኛው ሁለተኛ  አዛውንት እያመለከተ እሱ ደግሞ ‹‹ስኬት››  ይባላል። እሱ ደግሞ ማዕድ ከእናንተ ጋር የሚካፈል ከሆነ የጀመራችሁት ማንኛውም ጥረት ሁሌም ስኬታማ ትሆናላችሁ አላቸው። ከዚያም ወደ ራሱ እያመለከተ እኔ ደግሞ ‹‹ፍቅር›› እባላለሁ፣ ከአንተ ጋር ብሄድ ቤታችሁ ዘወትር በፍቅር ይሞላል። ብሎ ከሦስታችን ማን እንደሚገባ ከባለቤቷ ጋር እንዲወያዩ ነገራት። ባሏም ነገሩን በሰማ ጊዜ በጣም ተደስቶ። ‹‹ሀብት›› እንጋብዝ። እሱ ቢመጣ ቤታችንን በሀብት ይሙላ ሌላው ቀላል ነው ሲላት። ሚስቱ ግን አይሆንም ‹‹ስኬትን›› እንጋብዝ ስኬት ካለ ሀብት ይመጣል አለች። ልጃቸው ይህንን ሲነጋገሩ ትሰማ ነበርና። ለምን ‹‹ፍቅርን›› በቤታችን ብንጋብዝ ቤታችን ለዘላለም በፍቅር ይሞላል አለቻቸው።

ባልና ሚስት በልጃቸው ሐሳብ ተስማምተው። ሴቲቱም ‹‹ከእናንተ መካከል ፍቅር የትኛው ነው? እሱ ይግባና እንግዳችን ሁኑ አለች። ፍቅርም ተነስቶ ወደ ቤቱ መሄድ ሲጀመር ሁለቱ ሀብትና ስኬት ተነስተው ይከተሉት ጀመር። ሴትየዋ እንዴ አንዳችሁን ብቻ አልነበረም መጋበዝ የምትችሉት ያላችሁኝ? አሁን ግን ፍቅርን ብቻ ፈልጌ ብጋብዝ ለምን እናንተ ተከተላችሁ? አለቻቸው። ሽማግሌዎቹም ሀብትን ብትጋብዙ ኖሮ ፍቅርና ስኬት እንቀር ነበር፣ ስኬትን ብትጋብዙ ደግሞ ሀብትና ፍቅር እንቀር ነበር፣ ፍቅርን ስለጋበዛችሁ ግን ሁለታችን ሀብትና ስኬት ተከታትለን መጣን።  ፍቅር በሄደበት ቦታ ሁሉ እኛም አብረን እንሄዳለን አሉ። 

‹‹ፍቅር ባለበት ሁሉ ሀብትና ስኬት ይከተላሉ።››

ፍቅር ይስጠን!

ሠናይ ዕለት

  • ዓባይነህ አስፋው
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች