Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊ‹‹እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ...

‹‹እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል?›› ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

ቀን:

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፈተና ምንጭ ከሆኑት አንዱና አመቺ ሁኔታ የፈጠረው በመላው አገሪቱ ያለው አለመግባባት ነው ሲሉ  ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ተናገሩ።

ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የዘንድሮን የረክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔን ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግራቸው፣ የማኅበረሰቡ ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ እንዳይደለ፣ በአገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረሰቡ ፈተና ከሆነ ውሎ ማደሩን፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ አገራዊ አለመግባባት ነው ብለዋል፡፡

‹‹በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፣ መምህራን፣ ካህናት፣ ምዕመናን እና አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በሰላም ወጥቶ መግባትም አጠራጣሪ ሆኖአል፣ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፤›› ብለዋል።

- Advertisement -

ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች መሆኑን፣ የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከእሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሱ ፈተናዎች ተልዕኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት እንደሆኑባት ጠቁመዋል፡፡

መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መምጣታቸውን የገለጹት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ‹‹ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤›› ብለዋል፡፡

ቅዱስነታቸው አያይዘውም፣ ‹‹ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እሽቅድምድሙም አይሎአል፡፡ የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው፣ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ጉዳት እየደረሰባት ከመሆኑም በላይ ሰላሟና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል፤›› ብለዋል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የተቀመጡት ሰዎች በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም ያሉት ፓትርያርኩ፣ ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

‹‹ሁሉም ጓዳው ቢፈተሽ ከዚህ የተለየ ነገር አይገኝም፡፡ አንድነትንና ሰላምን ግቡ ያደረገ ግምገማን መገምገም፣ መወያየትና መመካከር፣ ሕግንና ሥርዓትን ማዕከል አድርጎ መሥራት ተመራጭ መፍትሔ ነው፤›› ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት አስከፊ በደል መፈጸሙን፣ አሁንም አለመቆሙን ያስታወሱት ፓትርያርኩ፣ በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርጎ እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ስለሚሆን፣ ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ሥራ መሥራት እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡

‹‹እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል?›› የሚለውን ጥያቄ ያነሱት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ለአገር ህልውናና ድነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መሥራት እንደሚጠበቅባት አስገንዝበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...