Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሕክምና ግብዓት ምርትና ፈጠራ ዓውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

የሕክምና ግብዓት ምርትና ፈጠራ ዓውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

ቀን:

የጤና ሚኒስቴር የአገር ውስጥ የሕክምና ግብዓትን የማምረት አቅም ለማሳደግ የሚረዳ የምርትና ጤና ፈጠራ (ኢኖቬሽን) ዓውደ ርዕይ በሰኔ አጋማሽ እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡

‹‹ጤናችን በምርታችን›› በሚል መሪ ቃል፣ ከሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ  በሚሌኒየም አዳራሽ የሚካሄደውን የአገር አቀፍ ዓውደ ርዕይ አስመልክቶ የጤና ሚኒስትር ደኤታ ፍሬሕይወት አበበ እንደገለጹት፣ መድረኩ የአገር ውስጥ አምራቾችን ለመደገፍ፣ በዘርፉ አዳዲስ ኢንቨስተሮችን ለመሳብ እንዲሁም የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት ያግዛል፡፡

መድረኩ የፈጠራ ባለቤቶች ሥራዎቻቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ ትስስር የሚፈጥሩበትና ልምድ የሚለዋወጡበት፣ እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማትና ባለሀብቶች በዘርፉ ያላቸውን አጋርነት ለማሳደግ የሚያመች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሕክምና ግብዓት አቅርቦት ከ90 በመቶ በላይ የሚሸፈነው ከውጭ በሚገባ ምርት መሆኑን የጠቀሱት ወ/ሮ ፍሬሕይወት ይህን ገጽታ ለመቀነስ በተሠራው ሥራ ውጤት መታየቱን ገልጸዋል፡፡

የሕክምና ግብዓት አቅርቦትን በአገር ውስጥ ለማሳደግ በተሠራው ሥራ ከስምንት በመቶ ወደ 37 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ሚኒስትር ደኤታዋ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የአገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት የገበያ ድርሻን ወደ 47 በመቶ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

 በኢትዮጵያ ከ25 በላይ የሚሆኑ መካከለኛና ትልልቅ የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓት አምራች ኩባንያዎች ተሰማርተው የሕክምና ግብዓትና መገልገያ መሣሪያዎችን በማምረት ለጤና ሥርዓቱ መጠናከርና የአገልግሎት ፍላጎትን በማሟላት በኩል ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ የተለያዩ ምርቶችን በማምረት በጤናው ዘርፍ መጋቢና ወሳኝ እንደሆኑ ነው የተናገሩት፡፡

ለስድስት ቀናት የሚካሄደውን ዓውደ ርዕይ የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ማኅበርና ከአርሜወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው፡፡

በዓውደ ርዕዩ ከ150 በላይ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ የሕክምና ግብዓት አምራቾች ምርቶቻቸውን እንደሚያቀርቡ፣ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...