Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህል‹‹ክቡር ልጆች...››

‹‹ክቡር ልጆች…››

ቀን:

‹‹የውጥረት መንስዔ ምንድን ነው? ብሎ ጠይቆ ምላሹንም ያስከተለው ‹‹ንቁ!›› የተሰኘ ድረ ገጽ ነው።  ካነሳቸው ነጥቦች መካከል ከልጆች ጋር የተያያዙት ይገኙበታል።

ልጆችም ውጥረት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል፣  አንዳንዶች በትምህርት ቤት ጉልበተኞች እንደሚያስቸግሯቸው፣ ሌሎች ደግሞ ቤት ውስጥ ችላ እንደሚባሉ፣ አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም ፆታዊ ጥቃት የሚሰነዘርባቸው ልጆችም እንዳሉ ይዘረዝራል።

 ‹‹ብዙ ልጆች የትምህርት ውጤትና የፈተና ጉዳይ ያስጨንቃቸዋል። አንዳንድ ልጆች ደግሞ ወላጆቻቸው በመፋታታቸው ምክንያት ቤተሰባቸው ይፈርሳል። ውጥረት ያለባቸው ልጆች ቅዠት ሊያስቸግራቸው፣ ትምህርት የመቀበል ችግር ሊኖርባቸው፣ የመንፈስ ጭንቀት ሊይዛቸው ወይም ከሰዎች ጋር መቀላቀል ሊከብዳቸው ይችላል። እንዲያውም አንዳንዶቹ ስሜታቸውን መቆጣጠር ይቸግራቸዋል። ውጥረት ያለበት ልጅ አፋጣኝ እርዳታ ያስፈልገዋል፤›› ሲልም ያስገነዝባል።

- Advertisement -

ይህ በየትኛውም አገር ያጋጠመ፣ የሚያጋጥም ለመፍትሔውም የሥነ ልቦናም ሆነ የሕፃናት ዕድገት ባለሙያዎች እየሠሩበት ያለ ነው። መሰንበቻውን ከልጆችና ወጣቶች ዕድገት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥናቶችን የሠሩት አቶ ብርሃኑ በላቸው አሰፋ፣ ‹‹ክቡር ልጆች፣ የልጆች ሥነ ልቦና ለመገንባትና የስሜት ስብራት ለመጠገን የሚረዱ ቁልፍ መንገዶች››  የተሰኘ አዲስ የቤተሰብ መጽሐፍ  በአማርኛና አፋን ኦሮሞ አዘጋጅተው ለአንባቢያን አቅርበዋል። 

የአጠቃላይ የሕፃናት ዕድገት (ሆሊስቲክ ቻይልድ ዴቨሎፕመንት)፣ እና በሥነ ማኅበረሰብ (ሶሽዮሎጂ) ሁለተኛ ዲግሪዎች ያሏቸው አቶ ብርሃኑ፣ በመጽሐፋቸው እንደገለጹት፣ ‹‹በልጅነት የሚፈጠር የስሜት ጠባሳ (Adverse Childhood Experiences) እንደ ጥላ ይከተላል፡፡ ይህ የስሜት ጠባሳ አስፈላጊውን ሕክምና ካላገኝ ልጅነትን አልፎ ትዳር ከተመሠረተ በኋላ የስሜት ጠባሳው የመገለጥ ዕድል አለው፡፡ የልጅነት የስሜት ጠባሳ በልጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ አዕምሮአዊ፣ ስሜታዊ፣ ማኅበራዊና ጤና ነክ ተፅዕኖዎች ያሳድራል፡፡ 

የመጽሐፉ አዘጋጅ በምሳሌነት ካቀረቧቸው ታሪኮች አንዱ የሚከተለው ነው።

‹‹አንዲት እናት ልጆቿን ብቻዋን ታሳድጋለች፡፡ የአስተዳደግ ዘይቤዋ ከሌሎች ወላጆች ለየት ይላል፡፡ ልጆቿ ከሰፈር ልጆች ጋር ተቀላቅለው ሲጫወቱ ዓይቼ አላውቅምና ሁሌም ጥያቄ ይፈጥርብኝ ነበር፡፡ ‹ልጆችሽ ከዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር ሲጫወቱ አይቼ አላውቅም› አልኳት፡፡ 

‹‹በልጅነቴ ብቸኛ ወንድሜን ያጣሁት ሠፈር ውስጥ በተወረወረ ድንጋይ ነው›› ወዲያውም ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።

‹‹በጣም አዝናለሁ፤ መጠየቅ አልነበረብኝም›› አልኳት።

‹‹እነዚህን ብርቅዬ ልጆች እንደ ወንድሜ ማጣት አልፈልግም፡፡ ውጭ እንደ ሌሎች ልጆች ቢጫወቱ ይሞቱብኛል ብዬ እፈራለሁ፤›› አለችኝ።

‹‹ሕክምና ያላገኘ የልጅነት ጠባሳ ጊዜ ጠብቆ በትዳር ሕይወትም ይገለጣል›› የሚለው ክቡር ልጆች መጽሐፍ፣ በተለያየ ተግዳሮት ውስጥ ለሚገኙ ልጆች የመፍትሔ ሐሳብ ይዞ ቀርቧል፡፡ በተለይም ልጆች የሚስተዋልባቸውን የሥነ ልቦና ጫና እና የስሜት ስብራት ይተነትናል። መጽሐፉ በጥናት በማስደገፍ የመፍትሔ ሐሳብን በተጨባጭ ያመላክታል ብሏል የመጽሐፉ ደራሲ።

በክቡር ልጆች ከተነሱት መካከል የልጅነት የስሜት ጠባሳ (Childhood Experiences)፣ ለልጆች ጊዜ መስጠት (Quality time)፣ የጨወታ ሕክምና (Play Therapy)፣ ልዩ ድጋፍ የሚሹ ልጆች፣ የቤተሰብ የስሜት ትስስር (Attachment) እና ሌሎችም ይገኙበታል። የቤተሰብ መጽሐፉ በልጆች ሥነ ልቦና ላይ ጥናትን መሠረት ያደረገ ብቻ ሳይሆን፣  አገራዊ ለዛ ያለው እውነተኛ ታሪኮችን የሚያስቃኝ መሆኑንም ደራሲው ጠቅሰዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...