Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ‹‹ፖለቲከኞች ላይ ቀዶ ጥገና ከማካሄድ የቀለለ ሥራ የለም››

‹‹ፖለቲከኞች ላይ ቀዶ ጥገና ከማካሄድ የቀለለ ሥራ የለም››

ቀን:

አራት የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች ምን ዓይነት ሰውን ኦፕራሲዮን ማድረግ እንደሚመርጡ እየተወያዩ ነበር፡፡

አንደኛው፣ ‹‹እኔ የቤተ መጻሕፍት ሠራተኞችን (ላይብረሪያኖች) ኦፕራሲዮን ማድረግ እመርጣለሁ፡፡ ሲከፍቷቸው ሁሉም አካሎቻቸው በፊደላት ቅደም ተከተል ተቀምጠው ይገኛሉ›› አለ፡፡

ሁለተኛው፣ ‹‹እኔ እንኳን የሒሳብ ባለሙያዎችን እመርጣለሁ፡፡ ሲከፍቷቸው አካሎቻቸው ቁጥር ተጽፈውባቸውና ተደራጅተው ነው የሚገኙት፡፡››

ሦስተኛው፣ ‹‹የኔ ምርጫ የኤሌክትሪክ ባለሙያዎችን ኦፕራሲዮን ማድረግ ነው፡፡ ሲከፍቷቸው ሁሉም አካሎቻቸው በቀለም ኮድ የምስጢር መለያ ተሰድረው ይገኛሉ፡፡››

አራተኛው፣ ‹‹በጣም ተሳስታችኋል፣ ወዳጆቼ፡፡ ፖለቲከኞች ላይ ቀዶ ጥገና ከማካሄድ የቀለለ ሥራ የለም›› አለ፡፡

ጓደኞቹ በመገረም ‹‹የነርሱ አካላት አቀማመጥማ መላ ቅጡ የጠፋ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ለምን ግን እነሱን መረጥክ?›› በማለት ጠየቁት፡፡

‹‹አንደኛ፣ ፈጣሪ ልብ አልፈጠረላቸውም፣ አንጀት የላቸውም፣ አከርካሪም እንዲሁ፡፡ በዚያ ላይ ጭንቅላታቸውና መቀመጫቸው ተለዋዋጮች ናቸው›› ብሏቸው እርፍ አለ፡፡

[ማጣጣሚያ፡- የቀዶ ጥገና ባለሙያው ማለት የፈለገው ፖለቲከኞች ጨካኞችና ርህራሔ የለሾች፣ እንዲሁም ወላዋዮችና ማሰቢያ አዕምሮ የሌላቸው ናቸው ነው፡፡]

  • አረፈ ዓይኔ ሐጐስ ‹‹ፖለቲከኞች እፈሩ ቀልድ እና ቁምነገር›› [2013]
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...