Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልየበጀት እጥረት የፈተነው የአኅጉሩ የባህል ዘርፍ

የበጀት እጥረት የፈተነው የአኅጉሩ የባህል ዘርፍ

ቀን:

የአፍሪካ አገሮች ቢያንስ ከበጀታቸው አንድ ፐርሰንቱን ለባህል ዘርፍ መዋል አለበት የሚል ሐሳብ ለአፍሪካ ኅብረት ጥያቄ ቀርቦ መግባባት ላይም ተደርሶ እስከ 2022 ዓ.ም. ወደ ተግባር ይገባል የተባለ ቢሆንም እስካሁን እንቅስቃሴ አለመታየቱ ተገልጿል።

ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው ሰላም የተባለው ፕሮጀክት፣ አገሮች በ2022 ዓ.ም. ከብሔራዊ በጀታቸው ቢያንስ አንድ ከመቶ ያህሉን ለኪነጥበብ፣ ባህልና ቅርስ ዘርፎች እንዲመድቡ ማግባባት ላይ ቢደርስም፣ በአፍሪካ አገሮች አስደረግኩት ባለው ጥናት መሠረት ለባህል የሚመደበው በጀት በጣም ዝቅተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

መሪዎች ተሰባስበው የሚወስኑት ጉዳይ ወደታች ወርዶ ይሠራና መስመር ይይዝ ዘንድ ብዙ ሥራን ይጠይቃል ያሉት የሰላም መሥራችና ዋና ዳይሬክተር  የሆኑት አቶ ተሾመ ወንድሙ ናቸው።

- Advertisement -

የአፍሪካ የባህል ዘርፍ ብዙ ችግር ያለበት ነው የሚሉት አቶ ተሾመ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሁሉም የአፍሪካ አገሮች ለባህል ያላቸው  በጀት በጣም አናሳ ሲሆን አንዳንዶቹ ከነ አካቴው የላቸውም ማለት ይሻላል ሲሉ ይገልጹታል።

ያለውን በጀትም በአግባቡ ለመጠቀም አልተቻለም ያሉት ዳይሬክተሩ ለዚህ ደግሞ ባለሙያዎቹን ወቅሰዋል፡፡ ምክንያቱም መንግሥት ለባህል ዘርፉ ምን ያህል በጀት እንዳለው ቢታወቅም እንዴትና በምን ሁኔታ እየተጠቀመበት እንደሆነ ግልጽ አለመሆን  አንዱ የችግሩ ምንጭ ስለመሆኑ አንስተዋል።

በባህል ዙሪያ ከኢትዮጵያ፣ ዑጋንዳ ዛምቢያና ዚምባቡዌ የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት እንዳደረጉና በጥናቱም በርካታ የአፍሪካ አገሮች ባህላቸውን ለማሳደግና ለማስተዋወቅ የበጀት እጥረት ማነቆ እንደሆነባቸው ገልጸዋል፡፡ የባህል ዘርፉ እንዴት እየሠራ ነው በጀቱስ እንዴት ይንቀሳቀሳል? ለማንስ ይደርሳል የሚለው መረጃ ያልተሟላና ያልተደራጀ መሆኑን በጥናቱ የታዩ ችግሮች ናቸው ተብሏል።

‹‹ኢትዮጵያ ታሪካዊ አገር ናት›› የሚሉት አቶ ተሾመ ከሌሎች አገሮች ልዩ የሆነ ባህል ያላት ብትሆንም፣ ያላትን ባህል ለሌሎች አገሮች ከማስተዋወቅ አኳያ ግን ብዙ የሚቀሩ ነገሮች እንዳሉ ያነሳሉ፡፡

ያልታወቁትን ከማሳወቅ ባሻገር በሌሎች ዘንድ በከፊል የሚታወቁ የአገር መገለጫ የሆኑትን ወደ ኢንዱስትሪ በመቀየር የበለጠ ማሳወቅና ተጠቃሚ መሆን እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የባህል ዘርፉ ወደ ኢንዱስትሪ መንደር ተቀላቅሎ ከአገራዊ ፋይዳው ባለፈ በአፍሪካና በዓለም መድረክ ጎልቶ እንዲወጣ መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ያሉት አቶ ተሾመ፣ መንግሥት በቂ በጀትን ከመመደብ ጀምሮ ለዕድገቱ በር ከፋች የሆኑ ፖሊሲዎችን ማዘጋጀት ሲችልና ባህልን መሠረት ያደረጉ የትምህርት ተቋማት ማስፋፋት ሲቻል ውጤት ይገኛል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ባህል በሚፈለገው ልክ ገና አልታወቀም ያሉት አቶ ተሾመ፣ እንዲያውም በውጭው ዓለም የሚነገረው ችግራችን፣ ያለን ደካማ ጎን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ‹‹እጃችን ላይ ያለውን ነገር ጥለን በሌለን ነገር ላይ እየደከምን ነው፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ ለአብነትም ኢትዮጵያ የምትታወቅበትን ኢትዮ ጃዝና የኢትዮጵያ ቡናን ተጠቅመን ሌሎች ባህሎቻችን በሚፈለገው ልክ ማስተዋወቅ ስንችል ነገር ግን ምንም አልተጠቀምንበትም ይላሉ፡፡

በአቶ ተሾመ አገላለጽ፣ የባህል ዘርፉ አሁን ካለበት አካሄድ ወጥቶ በፍጥነት እንዲያድግ ከተፈለገ መንግሥት ከገንዘብ ባሻገር በዕውቀት ላይ ፈንድ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ያለውን ዕምቅ የባህል ሀብት ወደ ገንዘብ የሚቀየርበትን ሁኔታ በደንብ አጥንቶ በመሥራት ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡

ሙዚቃን ጨምሮ በሌሎች ሴክተሮች ላይ የተጠናከረ የቅጅ መብት ፖሊሲ ቢኖርና በአጠቃላይ ባለው የባህል ፖሊሲ ላይ ውይይት ቢደረግ ለዘርፉ መሻሻል አስተዋጽኦ የጎላ ነው ይላሉ አቶ ተሾመ፡፡

የባህል ዘርፉ በገንዘብ በደንብ ካልተደገፈ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት በጣም አዳጋች ነው ያሉት አቶ ተሾመ በጥናቱ ላይ የታዩ ችግሮችም ከዚሁ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ባህል ከኢኮኖሚ ጥቅም ባሻገር ለሰላምና ለዴሞክራሲ እንዲሁም ለሥራ ፈጠራ ያለው ሚና ቀደም ሲሉ ከተደረጉ ጥናቶች የታየ ሲሆን፣ በቅርቡ ከአራቱ የአፍሪካ አገሮች በተደረገው ጥናት ደግሞ የበጀት ማነስና ያለው በጀት በአግባቡ አለመጠቀም የሚሉ ችግሮች ጎልተው ታይተውበታል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

ከጥናቱ በመነሳትም መንግሥታት በአፍሪካ ኀብረት በገቡት ቃል መሠረት ከበጀታቸው አንድ በመቶ የሚሆነውን ለባህል ዘርፍ በ2022 ዓ.ም. እንሰጣለን ባሉት መሠረት እንዲተገብሩ ግፊት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አንድ ከመቶ ብዙ ገንዘብ ነው የሚሉት ዳይሬክተሩ አሁን ላይ ያለው በጀት ግን ከ0.01 የማይበልጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባህል፣ ልማትና ዴሞክራሲ የበለጠ እንዲጠናከሩ የእርስ በርስ ትስስርም እንዲሰፋ በኢኮኖሚ መደገፍ ይገባዋል ያሉት ደግሞ በአፍሪካ የባህል በጀት እጥረትና ሊስተካከሉ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር በመሆን ጥናቱን ያካሄዱት አቶ ይስማ ጽጌ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል በገንዘብ እጥረት ምክንያት ጥናት ሊደረግባቸው የሚገቡ አፍሪካን እርስ በርስ ሊያስተሳስሩ የሚችሉ በርካታ ባህሎች ጥናት ሳይደረግባቸውና ሳይተዋወቁ የቀሩ መኖራቸውንም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን የባህል ሀብት ለሌሎች ማስተዋወቅ ይቅርና ራሳችንም ያላወቅናቸው ሀብቶች አሉን የሚሉት ተመራማሪው፣ ያልተገለጡ ባህሎችን ሸፍኖ ካስቀራቸው ችግር አንዱ የገንዘብ እጥረት ነው ሲሉ አመልክተዋ፡፡

‹‹የራስን ባህል ወደ ጎን ብሎ የውጭ ባህልን በመቀበልና በመከተል እንዲሁም የሌሎችን ባህል በማስተዋወቅ ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም፤›› የሚሉት አቶ ይስማ፣ በመጀመሪያ የራሳችንን ባህል በመያዝ የሌሎችን ማክበር ለባህል ትስስሩ መጎልበት ወሳኝ ነጥብ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...