Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹አልባሌውን ለኔ ስጡኝ››

ትኩስ ፅሁፎች

በቀደም እኛ ሠፈር እሚገኘው  መሬት አስተዳደር ቢሮ ጎራ ብየ ጎራው አልሁ፤

ከአስተዳዳሪው ጠረጴዛ ላይ፥ ሜትር፥ ችካልና በሶስት ጎድጓዳ ሳህኖች የተቀመጠ ናሙና አፈር ተደርድሮ ይታያል፤ 

‹‹ምን  እንርዳዎ ?›› አለኝ አስተዳዳሪው፤

‹‹የሆነች ቀለል ያለች   አምስት ሺ ካሬ መሬት ፈልጌ ነበር››

‹‹የገበሬ መሬት ነው የፈለጉት?››

‹‹ የወዛደርም ቢሆን አይደብረኝም፤››

‹‹አዝናለሁ፤ ለጊዜው የሚሸጥ መሬት የለንም››

‹‹እኔም የሚሸጥ ሳይሆን የሚሰጥ መሬት ነው የምፈልገው››

‹‹ምንስ ስለሆንክ ነው ላንተ መሬት የሚሰጥህ?››

ሰውየው  ካንቱ ወደ  አንተ የተሸጋገረበት ፍጥነት አስደነቀኝ፤

‹‹እስካሁን ለናት አገሬ ካደረግሁት አስተዋጽኦ አንፃር  መሬት ብቻ ሳይሆን ፥ የአየር ክልል ቢሰጠኝ አይበዛብኝም››

ሰውየው ዘበኞችን ለመጥራት ስልኩን ሲያነሳ፥ ወደ መስኮት እየጠቆምኩ፥

 ‹‹እዛ ማዳ  ታጥሮ የበሰበበሰ መሬት ምን ይሠራል?›› 

‹‹የወጣቶች የሥራ ፈጠራ ማዕከል ልንገነባበት ነው›› አለኝ፤

‹‹ከገነባችሁ በሁዋላስ?››

‹‹አልባሌ ቦታ የሚውሉ ወጣቶች ወደ ማዕከሉ እንዲገቡ ይደረጋል››

‹‹እሺ  አልባሌውን ቦታ ለኔ  ስጡኝ››  

በቀደም እኛ ሠፈር እኛ ሠፈር አስፋልት ዳር ያለ ሥጋ ቤት ባለቤት ጫማ ያስጠርጋል፤ እኔ ወረፋ እየጠብቅሁ ነው፤

‹‹ቅድምኮ  የግብረ ኃይሉ አባላት ሱቄን  በሜትር ለከትውት ሄዱ›› አለ ሥጋ ሻጩ፤

‹‹አይይ ! ሊያፐርሱት ነው ማለት ነው››  አለ ሊስትሮው፤

‹‹ሊያፈርሱት እንደሆነ በምን  አወቅህ?››

‹‹ታዲያ በሜትር የለኩት  ልብስ ሊያሰፑለት ነው?››

በእውቀቱ ሥዩም፣ ‹‹ከአልፎሂያጁ ማስታወሻ›› የተቀነጨበ

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች