Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የተሻለ ስካር ፍለጋ

ትኩስ ፅሁፎች

‹‹… ሰሞኑን ከቡና ቤት ወደ ቡና ቤት የተሻለ ስካር ፍለጋ እዘላለሁ፡፡ ከዚያም ሐረግ በለበሰ የግንብ አጥር ሥር እሸናለሁ፡፡ የሽንቴ አለቅጥ መርዘም ለብዙ ደቂቃ እንድቆም ያስገድደኛል፡፡ ይህም ልጅነቴን ያስታውሰኛል፡፡

አብዛኛውን ልጅነቴን ያሳለፍኩት ቆሜ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ምናልባትም ከአክሱም ሐውልት በቀር በመቆም የሚስተካከለኝ የለም፡፡ ማለዳ እነሳለሁ፣ ወደ ትምህርት ቤት እሄድና የባንዲራ መዝሙር እስኪያልቅ እቆማለሁ፡፡ የባንዲራ መዝሙሩን የጻፈው ሰውዬ በስንኝ ብዛት ተከፍሎታል መሰል አለቅጥ አስረዝሞታል፡፡

ከትምህርት በኋላ እናቴ ወደ ቤተ ክርስቲያን ትልከኛለች፡፡ በቅዳሴ ሰዓት አዛውንት ምዕመናን መቋሚያ ተደግፈው ወይም ግድግዳው ላይ ዘመም ብለው ጸሎት ሲያደርሱ አያለሁ፡፡ ባለመቆማቸው የሚቆጣቸው መልአክም ሆነ ካህን አልነበረም፡፡ እርጅና ጥቅም አለው ድካምን በገሃድ የመግለጽ መብት ያጎናጽፋል፡፡ ወጣቶችና ልጆች ግን ለሦስት ሰዓታት እንድንቆም እንገደዳለን፡፡ ለሦስት ሰዓት ያህል ቆመን እግራችን እንደሸንበቆ አለመሰበሩ እግዜር አለመኖሩ ማረጋገጫ ይመስለኛል፡፡

ከቤተ ክርስቲያን ወደ ቤት ስመለስ እናቴ ‹‹ና ወዲህ ልመርቅህ!›› ትላለች፡፡ ምርቃቷ እስኪያልቅ ድረስ ከባንዲራ መዝሙርና ከቅዳሴ የተረፈው ቅልጥሜ እየተንቀጠቀጠ በፊቷ እቆማለሁ፡፡ (በባህልም ሆነ በፖለቲካ መቆምን የአክብሮት ምልክት አድርጎ የፈጠረው ሰውዬ ቂጥ የሌለው መሆን አለበት ብዬ አማርር ነበር)፡፡

  • በዕውቀቱ ሥዩም ‹‹እንቅልፍና ዕድሜ›› (2000)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች