Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ክፉ ምላስ ለባለቤቱ ደመኛ ነው››

ትኩስ ፅሁፎች

‹‹አጤ ተክለ ጊዮርጊስ (1861-1863 ዘመነ መንግሥታቸው) ሦስት ዓመት ገዙ፤ አልነገሡም፡፡ ጎጃሜ ተጫወተባቸው፡፡ ‹የኛ ጌታ ሁነህ እንዲያው ‹ደጃች ጎበዜ› ስትባል ትኖራለህ?› አጤ ተባል እንጅ!’ አሏቸው ደጃች ጎሹ ብሩ፡፡

እንዲያው ዝም ብለው ዘቢጥ-ኸኛ አገር ሜዳ ላይ ነው – ‹አጤ ተክለ ጊዮርጊስ በል!› ኸሜዳው ላይ አጤ ተክለ ጊዮርጊስ ሆኑ፡፡ ዘቢጥ ላይ ‹አጤ በል!› ብለው አዋጅ ነገሩ፡፡

ጎሹ ብሩ በገዛ ሥራው ዘበተበት፤ ‹እንዲህ ነው! አቡን የለ፣ እጨጌ የለ፣ መቀባት የለ፣ እንዲያው አጤ!› ብሎ እዚያ ዘበተ፡፡

ዘቢጥ ላይ አባታቸው የተሰቀሉበት ነው (ያጤ ተክለ ጊዮርጊስ) (በአጤ ቴዎድሮስ ተይዘው መጥተው ዘቢጥ ላይ ኸግራር ተሰቀሉ፡፡) ዛድያ ‹እንዴ! የደጃች ጎበዜ አባት የተሰቀሉበት እያለ የከብት እረኛ ሁሉ መጠያየቂያ…› አህያ አላየህም ወይ ‹ደጃች – ከተሰቀሉበት ግራር አጠገብ ነበር ‹ጥጃ አላየህም ወይ?› …እንዲያው ያህያና የጥጃ መጠየቂያ ሁኖ፡፡ ‹ይቆረጥ አሉ፤› ተቆረጠ ኸሥሩ፤ አስቆረጡ፡፡

ኋላ ይኸው ጎሹ ብሩ ጎጃሜው እልፍ ብሎ ‹እንዲህ ነው! ልጅ እንዲህ ይወለድ፡፡ ደም ተመለሰ እኮ! አለ፡፡  ታድያ አሰቀሉት እሱን፡፡ ኸዚያው ዘቢጥ ይመስለኛል፡፡ ክፉ ምላስ ለባለቤቱ ደመኛ ነው፡፡››

  • መንግሥቱ ለማ ‹‹መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ››
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች