Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ምንያለ ነው! ሳልሞት ይፈታኛል!››

ትኩስ ፅሁፎች

ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ባል ሳይወጣላቸው  ነው የሞቱት ይባላል። በመጀመሪያ ገና በጨቅላነታቸው በዕድሜ አቻቸው  ያልሆኑ ራስ አርዓያ (የአፄ ዮሐንስን ልጅ) እንዲያገቡ ተደረገ። ራስ አርዓያ ከሞቱ በኋላ  ደግሞ  የሰሜኑን ኢትዮጵያ ፖለቲካ ለመጠበቅ ሲባል ለራስ ጉግሳ ተዳሩ።

ራስ ጉግሳ ብዙው  የሌሊት ጊዜያቸውን በጸሎት ያሳልፉት ነበር።  ንግሥት  ዘውዲቱ ለአቅመ  ሔዋን ደርሰው የወንድ ክንድ ተንተርሰው ለመተኛት በሚፈለጉበት አፍላ  የወጣትነት ዕድሜያቸው ሽማግሌው ራስ ጉግሳ ከሚስታቸው ይልቅ  ዳዊታቸውን ያስቀድሙ ነበር።

አንድ  ቀን ንግሥቲቱ  ባለቤታቸው  ከአሁን አሁን ጸሎታቸው ጨርሰው ከጎኔ ጋደም ይላሉ ብለው  ቢጠይቁም ጸሎታቸው አልጨርስ አሉ። በዚህን ጊዜ ዳዊት ይደግሙ ወደነበሩት ባላቸው እያፈጠጡ ‹‹ምን ያለው ነው ይህን ደግሞ ሳልሞት ይፈታኛል›› አሉዋቸው  ይባላል።

  • ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር ‹‹ኅብረ-ብዕር››
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች