Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየፓሪስ ኦሊምፒክ ዝግጅቶችን ችላ ያለው አገራዊው  የስፖርት ምክር ቤት

የፓሪስ ኦሊምፒክ ዝግጅቶችን ችላ ያለው አገራዊው  የስፖርት ምክር ቤት

ቀን:

በአገር አቀፍ ደረጃ የተመሠረተው ብሔራዊ የስፖርት ምክር ቤት፣ በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከተቋቋመለት ዓላማና ግብ አኳያ ‹‹ምን እየሠራ ነው?›› የሚሉ ጥያቄዎች መደመጣቸው አልቀረም፡፡

ምክር ቤቱ ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ስለቀረው የፓሪስ ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ትንፍሽ አለማለቱም ትችት አስከትሎበታል፡፡

ሚኒስቴሩ በትስስር ገጹ እንዳስነበበው ከሆነ፣ ባለፈው ሚያዝያ ብሔራዊ የስፖርት ምክር ቤቱ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ፣ የስፖርት ማኅበራት በሚቋቋሙበት መመሪያ ዙሪያ ከከተማ አስተዳደር የስፖርት ማኅበራት አደረጃጀት ኃላፊዎችና ከአገር አቀፍ የስፖርት ማኅበራት አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡

- Advertisement -

አጀንዳው በዋናነት የስፖርት ማኅበራት ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን በወጣው መመሪያ አተገባበር ሒደት ላጋጠሙ ችግሮች የመፍትሔ ሐሳቦችን ለማመላከት እንደሆነም ያስረዳል፡፡

ለውይይት መነሻ ያለውን ሰነድ በማዘጋጀት፣ ከፖሊሲ አንፃር የስፖርት አደረጃጀት ሁኔታን፣ ሚናን፣ መርሆዎች (መንግሥታዊና ሕዝባዊ አደረጃጀቶች)፣ ሕዝባዊ መሠረት ያላቸው የስፖርት ማኅበራት መቋቋም ከኢኮኖሚያዊ፣ ከማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታቸው፣ የስፖርት ማኅበራት አደረጃጀት ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራትን በማኅበራዊ አደረጃጀትና አሠራር አንፃር የታዩ ችግሮችን፣ የግብዓትና የፋይናንስ ችግሮችን፣ እንዲሁም ማኅበራቱ የሚያወጡዋቸውን መመሪያዎችና ደንቦች ተፈጻሚ ለማድረግ ያሉባቸውን ተግዳሮቶች፣ ማኅበራቱ በፋይናንስ ራሳቸውን ለመቻል ያሉባቸውን ችግሮች እንዲሁም የመፍትሔ ሐሳቦችን የዳሰሰ ሰነድ ስለመሆኑ ጭምር ያትታል፡፡

በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ያተተው መረጃው፣ በተለይም የብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ፕሬዚዳንቶችና የሥራ አስፈጻሚዎች የምርጫ ሕግና የሥራ ዘመን ላይ አተኩሯል፡፡

ይህን አካሄድ የተቹ አንድ ባለሙያ መመሪያው በተጠቀሱት የሥራ ኃላፊዎች ላይ የአገልግሎት ጊዜን ከመገደብ ይልቅ፣ በኃላፊነት ላይ የሚገኘው አመራር ወይም ግለሰብ ምን ሠራ? በሚል ቢታይ፣ እንደ አገር ኢትዮጵያ ከአኅጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የመሪነት ዕድል እንድታገኝ የሚያስችላት ስለመሆኑ ጭምር ያስረዳሉ፡፡

በተጨማሪም የክልል ክለቦችን ለማቋቋም ያለው የበጀት ችግርና በተጨባጭ የሱፐርቪዥን ሥራ መሠራት እንዳለበት ይጠቅሳል፡፡

ውይይቱን የመሩት የስፖርት ሚኒስትር ደኤታ መስፍን ቸርነት (አምባሳደር) ሲሆኑ፣ መመሪያው የሪፎርም ውጤት እንደሆነ፣ መንግሥት ስፖርቱን ለማልማት የሚያወጣቸው ሕግና መመሪያዎች መከበር ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

የብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ፕሬዚዳንቶችና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሚኒስቴሩ እተገብረዋለሁ ያለው የአገልግሎት ዘመን ገደብ ከዓለም አቀፍ ሕግና መመሪያ አንፃር የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት በግልጽ የሚያሳይ እንደሆነ በመግለጽ መመሪያውን ፈጽሞ እንደማይቀበሉ መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በተለይም ሚኒስቴሩ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥ ለማድረግ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ማንነታቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፌዴሬሽን አመራሮች በበኩላቸው ‹‹ወቅቱ በአንድም ሆነ በሌላ ለፓሪስ ኦሊምፒክ ዝግጅት በጋራ መነጋገርና መንቀሳቀስ ሲገባ፣ ያውም ለዓመታት ሲንከባበል የቆየን ጉዳይ በምክር ቤት ደረጃ አጀንዳ አድርጎ ለውይይት ማቅረብ ምን ይሉታል? በማለት ይጠይቃሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...