Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለትግራይ ክለቦች ማጠናከሪያ ብሔራዊ ቴሌቶን ተዘጋጀ

ለትግራይ ክለቦች ማጠናከሪያ ብሔራዊ ቴሌቶን ተዘጋጀ

ቀን:

በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ጦርነት ምክንያት ከፕሪሚየር ሊጉ ተለይተው የነበሩትና ዳግም ወደ ውድድሩ እንዲመለሱ የተወሰነላቸው የትግራይ ክለቦችን የሚያጠናከር ብሔራዊ ቴሌቶን መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡

የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ክለቦቹን በፋይናንስ ለመደገፍ ለሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተዘጋጀው ብሔራዊ ቴሌቶን ኅብረተሰቡ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ‹‹ክለቦቻችንን በፋይናንስ በመደገፍ ስፖርት የሰላም፣ ስፖርት የአንድነታችን፣ ስፖርት የማኅበራዊ ትስስራችን ታላቁ መሣሪያ እንደሆነ በተግባር እናረጋግጥ፤›› ብለዋል፡፡

በክልሉና በፌዴራል መንግሥት መካከል ጦርነት እስከተፈጠረበት ጊዜ ድረስ ይወዳደሩ የነበሩት ሦስቱ የትግራይ ክለቦች መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ ዓዲግራትና ስሑል ሽረ እንዳሥላሴ በፕሪቶሪያው ስምምነት ማዕቀፍ መሠረት በሚቀጥለው ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚካፈሉ ይሆናል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...